ሚያዝያ 4 2017 - ኢትዮ ቴሌኮም ተጨማሪ 114 ከተሞችን የዘመናዊው 4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረጉን ተናገረ
- sheger1021fm
- Apr 12
- 1 min read
ኢትዮ ቴሌኮም ከዚህ በፊት ከነበረው በተጨማሪ 114 ከተሞችን የዘመናዊው 4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረጉን ተናገረ።
በደቡብ ደቡብ ምስራቅ ሪጂን 56 ከተሞችን የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ ኔትወርክ አገልግሎት መጠቀም መጀመራቸውን ኩባንያው አስረድቷል።
በተመሳሳይ በደቡብ ምስራቅ ሪጂን 58 ከተሞች የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ ኔትወርክ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ጀምረዋል ተብሏል።

የአራተኛው ትውልድ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት ማግኘት የጀመሩት ተጨመሪ 14 ከተሞች በባሌ ዞን፣ አርሲ ዞን፣ ምስራቅ ባሌ ዞን፣ ምዕራብ አርሲ ዞን እና ምስራቅ ሸዋ ዞን የሚገኙ ከተሞች ናቸው።
ኩባንያው በትላንትናው እለት የባሌ ሮቤና የአርሲ ከተሞች የ5ጂ ኔትወርክ ማቅረብ መጀመሩን መናገሩ ይታወሳል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
📌Spotify : https://shorturl.at/QG8f2
Comentarios