top of page

ሚያዝያ 4፣2016 - የህዳሴ ግድብን አዲስ አበባ ላይ ለማሳየት የዛሬ 4 ዓመት ይገነባል የተባለው ሞዴል ፓርክ ግንባታ ዛሬም አልተጀመረም ተባለ

በጉባ የሚገኘውን የታላቁ የህዳሴ ግድብን አዲስ አበባ ላይ ለማሳየት የዛሬ 4 ዓመት ይገነባል የተባለው ሞዴል ፓርክ ግንባታ ዛሬም አልተጀመረም ተባለ፡፡


አለም ባንክ አካባቢ ይገነባል ተብሎ የነበረው ‘’ሞዴል ፓርክ’’ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ምን እንደሚመስል ቁልጭ አድርጎ ያሳያል ተብሎ የታሰበ መሆኑን ሰምተናል፡፡


የታሰበው ‘’ሞዴል ፓርክ’’ በተለይም የህዳሴው ግድብን በአካል ቦታው ድረስ ሄደው ማየት ለማይችሉ፤ ውሃው እንዴት እንደሚጣራ እና የግድቡን አጠቃላይ ገጽታውን ለማሳየት ታልሞ የታቀደ ፕሮጀክት እንደሆነም ተነግሯል፡፡


የማንያዘዋል ጌታሁን ያሰናዳውን በያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Comments


bottom of page