ሚያዝያ 3 2017 - ወደቀያቸው ከተመለሱ የትግራይ ተፈናቃዮች መካከል ለዳግም መፈናቀል የተዳረጉ መኖራቸውን ኢሰመኮ ተናገረ
- sheger1021fm
- Apr 11
- 1 min read
የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ወደቀያቸው ከተመለሱ የትግራይ ተፈናቃዮች መካከል ለዳግም መፈናቀል የተዳረጉ መኖራቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተናገረ፡፡
ይህም የሆነው በመፈናቀል ወቅት የተፈጠረ ቂምና ቁርሾ በእርቅና በውይይት እልባት አለማግኘቱ ስጋት ስለ ፈጠረባቸው ነው ሲል ተናግሯል፡፡
እዛ ያሉትም ቢሆኑ በቂ የምግብ ድጋፍ ስለማይቀርብላቸው ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ተጋልጠዋል ብሏል፡፡
በአካባቢው ማኅበረሰብ መካከል ያለው ግንኙነት ሰላማዊ ቢሆንም ጦርነቱን ተከትሎ በአማራ ክልል በኩል አካባቢውን ሲያስተዳድሩ በነበሩ አካላት እና ወደ አካባቢው በተመለሱ የትግራይ ክልል የፖለቲካ አመራሮችና የጸጥታ አካላት መካከል መፍትኤ ያላገኙ አለመግባባቶች እንዳሉም ሰምተናል።
ይህም በተመላሾች ደህንነት ላይ ሥጋት ፈጥሮሯል ተብሏል፡፡
ከመፈናቀላቸው በፊት በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ይሰሩ የነበሩ ተመላሾች አብዛኛዎቹ ወደ ሥራቸው ገበታቸው አለመመለሳቸውን ኢሰመኮ ተናግሯል፡፡
በጦርነቱ ወቅት ትምህርት ቤቶች የወደሙ እና በከፊል የፈረሱ በመሆኑ በራያ አላማጣ እና ዛታ ከጦርነቱ በኋላ በአብዛኛው የትምህርት አገልግሎት አልተጀመረም ተብሏል፡፡
በተለይም በአላማጣ ከተማ ከመፈናቀላቸው በፊት በቀበሌ ቤቶች ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ወደ አካባቢያቸው ሲመለሱ የቀበሌ ቤቶቹ ለሌሎች ሰዎች ተላልፈው እንደጠበቋቸው በተመሳሳይ የሌሎች ተመላሾች የግል መኖሪያ ቤቶች እና የንግድ ቦታዎች በሌሎች ሰዎች ተይዘው የሚገኙ መሆኑን ተመላሾች አስረድቷል፡፡
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
📌Spotify : https://shorturl.at/QG8f2
Comments