top of page

ሚያዝያ 3 2017 - ኢትዮ ቴሌኮም በባሌ ሮቤ እና አሰላ የአምስተኛውን ትውልድ (5G) የኢንተርኔት አስጀመረ።

  • sheger1021fm
  • Apr 11
  • 1 min read

ኢትዮ ቴሌኮም በባሌ ሮቤ እና አሰላ ከተሞች የአስተኛውን ትውልድ (5G) የኢንተርኔት አገልግሎት አስጀመረ።

 

ከዚህ በተጨማሪም በ114 የሪጅን ከተሞች የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት አስጀምሯል።


የዚሁ ፕሮግራም ማስጀመሪያ ስነስርዓት በባሌ  ሮቤ ከተማ በዛሬው እለት ተካሂዷል።


ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ እ.ኤ.አ. በ2022 የተጀመረው የ5ጂ ገመድ አልባ ቴክኖሎጂ በመላ ሀገሪቱ ወደሚገኙ ከተሞች እያስፋፋ  ሲሆን እስካሁን ድረስ ባሌ ሮቤና አሰላን ጨምሮ በ16 ትላልቅ ከተሞች አስጀምሯል።

አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ በጅግጅጋ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ባህር ዳር፣ ሐዋሳ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ሆሳዕና፣ አርባ ምንጭ፣ ቢሾፍቱ እና ጅማ፣ ደሴና ኮምቦልቻ ከተሞች አገልግሎቱን ቀደም ብለው ያገኙ ናቸው።


በዛሬው ዕለት አዲስ በተቋቋመው በደቡብ ደቡብ ምሥራቅ ሪጂን ባሌ ሮቤ እና በደቡብ ምስራቅ ሪጅን አሰላ ከተሞች ከተሞች የተጀመረው የ5ጂ አገልግሎት፣  ኢትዮጵያን የመጪው ጊዜ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንድትሆን ለማስቻል እንዲሁም የዲጂታል እና ዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶችን ተደራሽነት ለመጨመር ኩባንያው ያለውን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ ነው ተብሎለታል።


በባሌ ሮቤ ፦


• ዋቆ ጉቱ አደባባይ፣


• ሮቤ ኢትዮ ቴሌኮም ቢሮ (ነባሩ)፣


• ባሌ ዞን ትምህርት ቢሮ፣


• ሮቤ ቴክኒክ እና ሙያ ሥልጠና ኮሌጅ እና


• መደወላቡ ዩንቨርሲቲ ዋና ግቢ የአምስተኛው ትውልድ ኢንተርኔት  መጠቀም ችለዋል።


በአሰላ ከተማ ደግሞ፦


አሰላ ዞን አስተዳደር ቢሮ፣ 


• አሰላ ኢትዮ ቴሌኮም ቢሮ፣


• አሰላ ስታዲዮም፣


• አሰላ ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ እና


• አሰላ ትምህርት ቢሮ አካባቢዎች 5 G ማግኘት መቻል መጀመራቸው ተጠቅሷል።


የ5ጂ ቴክኖሎጂ እስከ 10 Gbps የሚደርስ ፍጥነት ያለው፣ ትእዛዝ የመቀበል ደረጃው (latency) እስከ 1 ሚሊ ሰከንድ የሚደርስ እና ቅጽበታዊ ሲሆን በአንድ ስኩዌር ኪሎ ሜትር እስከ 1 ሚሊዮን የቴሌኮም መሳሪያዎችን የማስተናገድ አቅም አለው ተብሎለታል ።


ይህ ቴክኖሎጂ በግለሰቦች፣ በድርጅቶች እና በኢንዱስትሪዎች በፍጥነት እያደገ የመጣውን የዳታ እና የኢንተርኔት ፍላጎት ለማርካት የሚያስችል ነው ተብሏል።


5ጂ የንግድ ሥራዎችን ለማዘመን፣ ቅልጥፍናን ለማሻሻል እና ፈጠራን እንደሚያበረታ ተነግሯል።


ንጋቱ ሙሉ

Kommentare


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page