top of page

ሚያዝያ 3፣2016 - ወረቀት አልባ የግዢ ስርዓት በ 169ኙም የመንግስት ባለበጀት መስሪያ ቤቶች ስራ ላይ ውሏል ተባለ

ወረቀት አልባ የግዢ ስርዓት በ 169ኙም የመንግስት ባለበጀት መስሪያ ቤቶች ስራ ላይ ውሏል ተባለ።


ቀጣዩ ስራ ለመስሪያ ቤቶቹ ተጠሪ ወደ ሆኑ ተቋማት እና ክልሎች አሰራሩን ማስፋት እንደሆነ የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን ተናግሯል።


ባለስልጣን መ/ቤቱ ይህንኑ እየተቆጣጠረ እንደሚገኝ ከዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሃጂ ኢብሣ ሠምተናል።


የግዢ ስርአቱ ስራ ላይ የዋለው በዋና ዋና የመንግስት ባለበጀት መስሪያ ቤቶች እንደሆነ ያስታወሱት ዳይሬክተሩ፤

በቀጣይ በተጠሪ ተቋማቶችም ለመተግበር ታስቧል ብለዋል።


ከፌዴራል ተቋማት በተጨማሪ የግዢ ስርአቱን ስራ ላይ ማዋል የጀመሩ ክልሎች እና የከተማ አስተዳደርም እንዳሉ የሰማን ሲሆን ከእነዚሀም መካከል የሲዳማ ክልል እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተጠቅስዋል።


አሰራሩ አልፎ አልፎ ከሚገጥሙት ጥቃቅን ችግሮች በስተቀር በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ ነግረውናል።


ወረቀት አልባ የሆነውን የግዢ ሰርአት መከተል ለቁጥጥር እና አሰራር አመቺ ይሆናል የሚል እምነት እንዳለው የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን ተናግሯል፡፡


ንጋቱ ረጋሣ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Telegram: @ShegerFMRadio102_1




Kommentare


bottom of page