top of page

ሚያዝያ 29 2017 - በቴክኒክና ሞያ ተቋማት ውስጥ ክህሎት ያለው የመምህር እጥረት ከፍተኛ መሆኑን የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ያደረገው ጥናት አሳየ፡፡

  • May 7, 2025
  • 1 min read

በቴክኒክና ሞያ ተቋማት ውስጥ ክህሎት ያለው የመምህር እጥረት ከፍተኛ መሆኑን የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ያደረገው ጥናት አሳየ፡፡


በተለይም ከዩኒቨርሲቲ ተመርቀው በቴክኒክና ሞያ የሚያስተምሩ መምህራን በኢንዱስትሪዎች የመስራት ልምድ ስለሌላቸው በሞያው የክህሎት እጥረት እንደሚታይባቸው ጥናቱ ጠቅሷል፡፡


የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ‘’የቴክኒክና ሞያ ትምህርትና ስልጠና ሥርዓት ግንባታ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ሽግግር’’ በሚል ርዕስ ነው ጥናቱን ያደረገው፡፡


በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት መሪ ተመራማሪ የሆኑት እና በዚህ ጥናት ከተሳተፉ ባለሞያዎች መካከል አማረ ማተቡ(ዶ/ር) አንዱ ናቸው፡፡


ከቴክኒክና ሞያ ሰልጥነው የሚወጡ ባለሞያዎች የክህሎት ማነስ እንደሚታይባቸው አምራች ተቋማት ነግረውናል ብለዋል፡፡


ከዚህ ባለፈም በዘርፉ ተሰማርተው ከሚያስተምሩ መምህራን መካከል የተግባር ተኮር የስራ ልምድ የሌላቸው መምህራን አሉ የተባለ ሲሆን ይህም ክህሎትና ጥራት ያለው ሰልጣኝ ለማፍራት በሚደረገው ጥረት ላይ ዋንኛ ችግር መሆኑን ዶክተር አማረ ነግረውናል፡፡


ከዚህም ባለፈ በቴክኒክና ሞያ ተቋማት ለተግባር መማሪያ ተብለው የተገዙ ቁሳቁሶች ዘመኑ እየሄበት ካለው ቴክኖሎጂዎች ጋር የሚጣጣም አይደለም ይህም ሰልጣኙ ወደ ስራው አለም ሲገባ አዲሱን ቴክኖሎጂ ለመላመድ እንዲቸገር እንደሚያደርገው ጥናቱ ያስረዳል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..


በረከት አካሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…






Recent Posts

See All
በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ሃዲዶች ላይ ለአካል ጉዳተኞች የተሰራው መወጣጫ(ራምፕ) ለዓመታት በመዘጋቱ አካል ጉዳተኞች ባቡር መጠቀም  ለማቆም ተገደናል ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ነሐሴ 7 2018 በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ሃዲዶች ላይ ለአካል ጉዳተኞች የተሰራው መወጣጫ(ራምፕ) ለዓመታት በመዘጋቱ አካል ጉዳተኞች ባቡር መጠቀም ለማቆም ተገደናል ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል። የሃዲዱ ጠባቂ የፀጥታ አካላት የተዘጋውን መወጣጫ(ራምፕ) እንዲከፍቱላቸው ቢጠይቁም የተሰጣቸው ምላሽ እስከ ድብደባ የደረሰ

 
 
 
የነሐሴ 7 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ዩጋንዳ ዩጋንዳ ከአውሮፓ የሚባረሩ የ3ኛ አገር ስደተኞችን ልትቀበል ነው ተባለ፡፡ ዩጋንዳ ከአውሮፓ ተባራሪዎቹን ተቀብላ ለማስተናገድ መዘጋጀቷን ካቲሜሪኒ የተሰኘ የግሪክ ጋዜጣ መዘገቡን አናዶሉ ፅፏል፡፡ ጋዜጣው ዘገባውን ያሰራጨው ዲፕሎማሲያዊ ምንጮችን በዋቢነት በመጥቀስ እንደሆነ ታውቋል፡፡ የሐሳቡ ቀዳሚ አፍላቂዎች

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page