top of page

ሚያዝያ  29፣2016 - ኢትዮጵያ በህዋ ላይ የ5 ዓመት ቆይታ የሚኖራት ሳተላይት ለማምጠቅ የጨረታ ሂደት ማጠናቀቋ ተነገረ

  • sheger1021fm
  • May 7, 2024
  • 1 min read

ኢትዮጵያ በህዋ ላይ የአምስት ዓመት የዕድሜ ቆይታ የሚኖራት ሳተላይት ለማምጠቅ የጨረታ ሂደት ማጠናቀቋ ተነገረ፡፡


ይህ የተነገረው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የ9 ወር የስራ አፈፃፀሙን ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ባቀረበበት ወቅት ነው፡፡


ለሶስተኛ ጊዜ ኢትዮጵያ ለማምጠቅ የጨረታ ሂደት ያጠናቀቀችባት ሳተላይት ስያሜዋ ኢቲ አር ኤስ 2 ናት ተብሏል፡፡


የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ ኢቲአር ኤስ 2 የተሰኘች ሳተላይት ለማምጠቅ የጨረታ ስራው ተጠናቆ በቴክኒክ ግምገማ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

የአሁኗ ሳተላይት በ2012 እና በ2013 ታህሳስ ወር ላይ መጥቀው አገልግሎታቸው ካበቃው 2 ሳተላይቶች በህዋ ቆይታዋም በአገልግሎቷም የተሸለች መሆኗን ተነግሯል፡፡


በህዋ ላይ አምስት ዓመት ትቆያለች የተባለችው ኢቲ አር ኤስ 2 ሳተላይት፤ ከበፊቶቹ የተሻለ አገልግሎት ይዛ ትመጣለች ተብሏል፡፡


በህዋ ላይ አምስት አመት መቆየቷ፣ ከሌሎች 3 ሳተላይቶች ጋር መረጃ መለዋወጥ መቻሏ፣ የተሻለ መረጃ እና ዳታ መስጠት መቻሏ ከቀድሞዎቹ የተሻለች ያደርጋታል ሲሉ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ ተናግረዋል፡፡


ከዚህ በፊት መጥቀዉ አገልግሎታቸዉ የተጠናቀቀው ሁሉቱ ሳተላይቶች ምን ፋይዳ አመጡ፤ የተባሉት ሚኒስትሩ 26.4 ቴራ ባይት መጠን ያለዉ የሳተላይት የመሬት ምልከታ መረጃ መፍጠር ተችሏል ብለዋል፡፡


የህዳሴ ግድብ ግንባታ የደን ምንጣሮ ቦታዎችን ለመየት የድን  እና የሰብል ሽፋን ለማወቅ እና ሌሎች አገልግሎቶችን ሰጥተዋል ሲሉ ሰምተናል፡፡


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





ความคิดเห็น


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page