top of page

ሚያዝያ 24፣2016 - በገበታ ለሀገር የተገነቡ ሎጆችን ስራ የማስኬድ ተግባርን የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዲወጣ ሃላፊነት ተሰጠው፡፡

በገበታ ለሀገር የተገነቡ ሎጆችን ስራ የማስኬድ ተግባርን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በስካይ ላይት ሆቴል ተቋሙ በኩል እንዲወጣ ሃላፊነት ተሰጠው፡፡


ለኢትዮጵያ አየር መንገድ በሃላፊነት መሰጠቱም የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ ከማስቻሉም ባለፈ ለአለም አቀፍ የቱሪዝም መዳረሻነት ትውውቅ ከፍ ያለ ዕድል ይፈጥራል ተብሏል።


በ'ገበታ ለሀገር' ስር የተሰሩ ፕሮጀክቶቹን ለአማራ፣ ለኦሮሚያ እና ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች እንዲረከቧቸው መደረጉ ተሰምቷል፡፡


ርክክቡም ዛሬ ጥዋት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በተዘጋጀ መርሃ ግብር መከናወኑ ተሰምቷል፡፡

የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች የሆኑት ሃላላ ኬላ ሎጅ፣ ጨበራ ጩርጩራ የዝሆን ዳና ሎጅ እና ወንጪ ኢኮ ሎጅ በቅርቡ መመረቃቸው የሚታወስ ሲሆን የጎርጎራ ፕሮጀክት ስራም በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ተናግሯል።


የ’ገበታ ለሀገር’ ስራ የብሔራዊው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አንዱ ማዕዘን የሆነውን ቱሪዝምን የማሳደግ አላማ እንዳለው ጽ/ቤቱ አስረድቷል።


ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page