top of page

ሚያዝያ 22 2017 - የመንግስት አካላት በተደጋጋሚ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ዳተኛ ሆነዋል ሲል ኢሰማኮ ተናገረ፡፡

  • Apr 30, 2025
  • 2 min read

በኢትዮጵያ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወሰን እንዲሁም እስከ 35 በመቶ የደረሰው ከደመወዝ ላይ የሚቆረጠው ግብር እንዲቀንስ ከዚህ ቀደም ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ በተዋረድ ያሉ የስራ ሃላፊዎችን ቢጠይቅም እስካሁን ሁነኛ ምላሽ እንዳላገኘ የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮምፌደራሽን (ኢሰማኮ) ተናግሯል፡፡


በጉዳዩ ዙሪያ #ኢሰማኮ ከ1ዓመት ከ6 ወር በፊት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ተወያይቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ይህንን ተከትሎም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመለከታቸውን የመንግስት አካላት በጉዳዩ ላይ ጥናት አድርገው እንዲያቀርቡ አቅጣጫ ሰጥተው ነበር በሏል ኮንፌደሬሽኑ፡፡


ጥናት እንዲከወን አቅጣጫ ቢሰጥም፤ ምላሽ ባለማግኘታችን ጠቅላይ ሚኒስትሩን በድጋሚ በደብዳቤ ለመጠየቅ ተገድደናል ሲል ባሳለፍነው ጥቅምት ወር 2017ዓ.ም ማለትም ከ6 ወራት በፊት ኮንፌደሬሽኑ ተናግሮ እንደነበርም ይታወሳል፡፡


ጥያቄዎቹ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተቀባይነት እንዳገኙ የሚጠቅሱት የኢሰማኮ ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ፤ በስም ያልጠቀሷቸውን ጥናቱን ከውኑ የተባሉ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ከምን ደረሰ ብለን በተደጋጋሚ ደጅ ብንጠናም ምናሽ አጥተናል ይላሉ፡፡


እንደ ሃላፊው አነጋገር ዝቅተኛ የደሞዝ ወለልን ለመወሰን ጥናት አንዲከውን ሃላፊነት የተሰጠው የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ነው፡፡ ይሁንና ለሚቀርብለት መሰል ጥያቄ በጥናት የምመልሰው ነው ከማለትና ከኮንፌደሬሽኑ ጋር ካደረገው የተወሰነ ንግግር ውጪ ጥናቱ በምን ደረጃ ላይ እንዳለ ከሚኒስቴሩ የተሰማ ነገር የለም፡፡

ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል መወሰን እንደ ሃገር በልቶ ማደር የሚችል እንዲኖር እንደሚያስችልና ምርታማነትን እንደሚጨምር የኢሰማኮ ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ጠቅሰው ኮንፌደሬሽኑም በጉዳዩ ዙሪያ የበኩሉን ጥናት እየከወነ ነው ሲሉም አስረድተዋል፡፡


ሌላውና በኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮምፌደራሽን በተደጋጋሚ ሲጠየቅ የነበረው እስከ 35 በመቶ የደረሰው ከደሞዝ ላይ የሚቆረጠው ግብር እንዲቀንስ ነው፡፡

በተለይም በጣም ዝቅ ያለ ደሞዝ የሚከፈላቸው ሰራተኞች በኑሮ ውድነቱ ምክንያት በልቶ ማደር እየከበዳቸው በመሆኑ በዚህም ላይ ጥናት እንዲያደርጉ አቅጣጫ የተሰጣቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች አሉ፤ ጉዳዩን ከዳር ለማድረስ ኢሰማኮ ግፊት እያደረገ ነው ብለዋል አቶ ካሳሁን፤ይሁንና ምን ያህል ርቀት እንደተጓዙ በዝርዝር ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡


የተጠየቁ ጥያቄዎች መልስ እስከሚያገኙ ድረስ ግፊት ማድረጋችንን እንቀጥላለን ያለው ኮንፌደሬሽኑ አካሄዳችን ግን ጥንቃቄ ተሞላበት ይሆናል ማለቱን ከሃላፊው ሰምተናል፡፡


ምንታምር ፀጋው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…






Recent Posts

See All
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የህፃናት እንክብካቤ ማዕከላት ወይም ማቆያዎች ላይ ለውጦች እየመጡ ነው ተባለ፡፡

ሐምሌ 15 2018 በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የህፃናት እንክብካቤ ማዕከላት ወይም ማቆያዎች ላይ ለውጦች እየመጡ ነው ተባለ፡፡ ከጥቂት አመታት በፊት የህፃናት ማቆያዎቹ ጥቂት ነበሩ ያለው የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት አሁን ላይ ከፍተኛ መሻሻሎች ታይተውበታል ብሏል፡፡ ጥናቱም በግል እና በመንግስት ማ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page