ሚያዝያ 22 2017 - ''አንዳንድ አሰሪዎች፣ የማህበር መሪዎች ለአባሎቻቸው መብት ስለተከራከሩ ብቻ ከስራ ይባረራሉ'' ኢሰማኮ
- sheger1021fm
- Apr 30
- 1 min read
በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵዊያን ሰራተኞች የኑሮ ሁኔታ፤ አሁንም አሳሳቢነቱ ቀጥሏል ሲል የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ተናገረ፡፡
ኮንፌዴሬሽኑ በመጪው ሀሙስ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ136ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረውን የሰራተኞች ቀንን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
ኢሰማኮ በመግለጫውም የዋጋ ግሽበት የደመወዝ ተከፋዩን የመግዛት አቅም በእጅጉ እንዳዳከመው ነውም ብሏል፡፡
ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እስካሁን አለመወሰኑን ያስታወሰው ኮንፌዴሬሽኑ ሰራተኞች የሚከፈላቸው ደመወዝ አነስተኛ ሆኖ እያለ ከፍተኛ የገቢ ግብር ስለሚቆረጥባቸው መሰረታዊ ፍላጎታቸውን እንዳያሟሉ አድርጓቸዋል ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ አንዳንድ አሰሪዎች፣ የማህበር መሪዎች ለአባሎቻቸው ስለቆሙ ወይም ለአባሎቻቸው መብት ስለተከራከሩ ብቻ ከስራ ይባረራሉ፣ ይዋከባሉ ወይም ራቅ ወዳለ ቦታ እንዲዘዋወሩ ይደረጋሉ ብለዋል፡፡
አቶ ካሳሁን ኑሮ የከበዳቸውን ተቀጣሪ ሰራተኞችን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተላኩ ጥያቄዎችን በተመለከተ በተደረገው ውይይት ጥያቄያችን ተቀባይነት አግኝቶ ለሚመለከታቸው ሚኒስትሮች ተላልፎ ተሰጥቷቸዋል፤ ሆኖም የተወሰኑ ጥያቄዎች ምላሽ ያገኙ ቢሆንም መሰረታዊና ቁልፍ የሆኑ የሰራተኛ ጥያቄዎች አልተመለሱም ብለዋል፡፡
ፍቅሩ አምባቸው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Commentaires