ሚያዝያ 22 2017 - በመጪዎቹ 10 ቀናት በአዲስ አበባ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል ተባለ፡፡
- sheger1021fm
- Apr 30
- 1 min read
በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች ከፍ ያለ ከባድ መጠን ያለው #ዝናብ ሊመዘገብ እንደሚችልም ተነግሯል፡፡
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት በመጪዎቹ 10 ቀናት የሚኖረውን የአየር ሁኔታ ትንበያ መረጃን ይፋ አድርጓል፡፡
በኢንስቲትዩቱ አሃዛዊ የትንበያ መረጃ መሰረት በአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረሪ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ የኦሮሚያ፣ የሶማሌ፣ የአማራ፣ ትግራይ እና ጋምቤላ አንዳንድ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ዝናብ በቀጣዮቹ ቀናት ይኖራቸዋል፡፡
በደቡብ ፣ በደቡብ ምስራቅ ፣ በምስራቅ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚሊ ሜትር በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ለመዘገብ ይችላልም ብሏል የተቋሙ መረጃ፡፡
አሃዛዊ የአየር ትንበያ መረጃው ከነገ ሚያዚያ 23 ቀን እስከ ግንቦት 2 ያሉትን 10 ቀናት የተመለከተ ነው ተብሏል፡፡
ቴዎድሮስ ወርቁ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
Comments