ሚያዝያ 21 2017 - የፌዴራል መ/ቤቶች አጀንዳዎቻቸውን ለምክክር ኮሚሽን የሚያቀርቡበት የምክክር መድረክ ግንቦት 8/2017 በአዲስ አበባ መካሄድ ይጀምራል ተባለ
- sheger1021fm
- Apr 29
- 1 min read
የህዝብ ተወካዮች፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት፣ የመከላከያ ሰራዊትን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራል መስሪያ ቤቶች አጀንዳዎቻቸውን ለምክክር ኮሚሽን የሚያቀርቡበት የምክክር መድረክ ግንቦት 8/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ መካሄድ ይጀምራል ተባለ፡፡
ለተከታታይ ሶስት ቀናት በአዲስ አበባ ይካሄዳል በተባለው የፌዴራል ባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ላይ የመከላከያ ሰራዊት እና የፌዴራል ፖሊስ በተወካዮቻቸው በኩል አጀንዳዎቻቸውን ለምክክር ኮሚሽን እንደሚያቀርቡ ተነግሯል፡፡
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ቃል አቃባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ ከሳምታት በኋላ መካሄድ በሚጀምረው የምክክር መድረክ ላይ የህግ አውጪው፣ ህግ ተርጓሚው እና ህግ አስፈጻሚው አካላት በምክክሩ ይሳተፋሉ፤ አጀንዳዎቻችን ናቸው ያሉትንም ለኮሚሽኑ ያስረክባሉ ብለን እንጠብቃለን ብለዋል፡፡
መድረኩ፤ ሀገራዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ የሀይማኖት፣ የፀጥታ፣ የፍትህ ተቋማት እና ሌሎች የፌዴራል ተቋማት ለሶስት ቀናት መክረው አጀንዳዎቻቸውን የሚያቀርቡበት ነው ያሉት ቃል አቀባዩ ከዚህ በፊት በክልሎች እና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የተሳተፉ የህብረተሰብ ከፍሎች በዚህኛው መድረክ አይሳተፉም ሲሉ አስረድተዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በተካሄዱ የምክከር መድረክ ላይ የተሳተፉ የህብረተሰብ ከፍሎች ማለትም የሃይማኖት ተቋማት፣ የንግድ ማህበረሰብ፣ የእድር፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የመምህራን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የአካል ጉዳተኞች እና የተፈናቃይ ህብረተሰብ ተወካዮች አጀንዳዎቻቸውን ማስረከባቸውን የጠቆሙት አቶ ጥበቡ ታደሰ በፌደራል ባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ላይ ግን እነዚህ አካላት እንደማይሳተፉ ነግረውናል፡፡
በሌላ በኩል ከትግራይ ክልል ውጭ ከሁሉም ከልሎች እና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች አጀንዳ ሰብስቦ ያጠናቀቀው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከኢትዮጵያ ውጭም በርካታ ኢትዮጵያውን በሚኖሩባቸው አካባቢዎች ተዘዋውሮ አጀንዳዎችን ለመቀበል በዝግጅት ላይ መሆኑን ተናግሯል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
Comments