top of page

ሚያዝያ 20 2017 - በሁሉም ወረዳዎች ውስጥ፤ ኢንዱስትሪዎች እንዲገነቡ ያለመ ስራ መጀመሩ ተነገረ

  • sheger1021fm
  • Apr 29
  • 1 min read

በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሁሉም ወረዳዎች ውስጥ፤ ኢንዱስትሪዎች እንዲገነቡ ያለመ ስራ መጀመሩ ተነገረ፡፡


ይህም በገጠር ያሉ ዜጎች ዳቦ ወይም ሌላ የሚፈልጉት ምርትን ለመግዛት ወደ ከተማ እንዳይወጡ ይረዳቸዋል ተብሏል፡፡


በሀገሪቱ ያሉ ወረዳዎች በየአካቢያቸው እንደሚያገኙት የግብዓት ዓይነት፤ እያንዳንዳቸው እስከ 3 ኢንዱስትሪዎች እንዲኖራቸው እየተሰራ መሆኑ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ተናግሯል፡፡


በዚህም ባለፉት 9 ወራት 206 ኢንዱስትሪዎች በገጠሪቱ የሀገሪቱ ክፍሎች መቋቋማቸውን የጠቀሰው ተቋሙ፤ ቁጥራቸውን ለማሳደግ በብርቱ መስራቴን እቀጥላለሁ ብሏል፡፡



በገጠር አካባቢዎች ኢንዱስትሪዎች ማስፋፋት የአካባቢው ነዋሪዎች ምርት በቀላሉ እንዲያገኙ ከማድረጉም በተጨማሪ፤ የስራ እድል በመፍጠር ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገው ፍልሰት ይቀንሳል ሲባልም ሰምተናል፡፡


ባለፉት ዘጠኝ ወራትም በሀገር ዓቀፍ ደረጃ 151,000 ሰዎች በመካከለኛ እና በአነስተኛ ኢንዱስትሪዎች ስራ አግኝተዋል ሲሉ የኢትዮጵያ የኢንተርፕራይ ልማት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አብዱልፈታ የሱፍ ተናግረዋል፡፡


የኤልክትሪክ ሀይል በበቂ አለማግኘት፣ የፋይናንስ አቅርቦት ችግር፣ የአስፈፃሚ አካላት አለመናበብ፣ በጥራት ማምረት አለመቻል እና ሌሎች የመሰረተ ልማት ችግሮች የአምራች ዘርፉን እየፈተኑ ያሉ ችግሮች እንደሆኑም ሀላፊው  ጠቅሰዋል፡፡


ችግሮች ቀንሰው ምርት እንዲጨምር፣ ከሚመለከታቸው ጋር እየሰራን ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡


በእዚህም ስራ፤ ስራ አቁመው የነበሩ 518  ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ እንዲመለሱ ተደርጓል ብለዋል፡፡


ከእነዚህ በተጨማሪም 2,752 አዳዲስ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ተከፍተዋል ሲለም ተናግረዋል አቶ አብዱልፈታ የሱፍ፡፡


ከዉጪ የሚገቡ ምርቶችን በመቀነስ በኩልም 1.6 ቢሊየን ዶላር ወጪ ከመሆን እንዲተርፍ ሆኗል ያሉት ሀላፊው ወደ ውጪ ከተላኩ ምርቶች ደግሞ 57 ሚሊየን ዶላር የዉጪ ምንዛሪ መገኘቱንም ተነግሯል፡፡


ለአምራቾች በ9 ወሩ የተሰጠው የብድር መጠን 6 ቢሊየን ብር መሆኑንና ከዚህ ውስጥም 95 በመቶው መመለስ መቻሉንም ተጠቅሷል፡፡

ማንያዘዋል ጌታሁን

Kommentare


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page