top of page

ሚያዝያ 2 2017 - የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በኤጀንሲዎች ወደ ውጭ ሀገር ለስራ ከሚላኩ ዜጎች ለማግኘት ካቀደው የውጭ ምንዛሪ፤ ማሳካት የቻለው 24 በመቶ ብቻ እንደሆነ ተናገረ

  • sheger1021fm
  • Apr 10
  • 1 min read

የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በኤጀንሲዎች ወደ ውጭ ሀገር ለስራ ከሚላኩ ዜጎች ለማግኘት ካቀደው የውጭ ምንዛሪ፤ ማሳካት የቻለው 24 በመቶ ብቻ እንደሆነ ተናገረ፡፡


ሚኒስቴሩ ይህን የተናገው ዛሬ የ9 ወር የስራ ክንውኑን ሪፖርቱን ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ባቀረበበት ወቅት ነው፡፡


ሚኒስቴሩ 472.5 ሚሊዮን ዶላር ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት አቅዶ ማሳካት የቻለው 113.4 ሚሊዮን ዶላር እንደሆነ እና ይህም የእቅዱን 24 በመቶ እንደሆነ ሪፖርቱን ያቀረቡት የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሙፈርያት ካሚል ተናግረዋል፡፡


113.4 ሚሊዮን ዶላር የተገኘው 943 ኤጀንሲዎች ወደ ውጭ አገር ከላኳቸው ዜጎች እንደሆነም አስረድተዋል፡፡


ሪፖርት ባላቀረቡ 221 ኤጀንሲዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ አንደተወሰደም በሪፖርቱ ቀርቧል፡፡


በሌላ በኩል በውጭ ሀገር የተሰማሩ ዜጎችን መብት በተመለከተ 804 አቤቱታዎች ቀርበው 719 አቤቱታዎች በመስማማት ተፈተው 85 ደግሞ በሂደት ላይ ይገኛሉ ተብሏል፡፡


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page