top of page

ሚያዝያ 2 2017 - ባቡር ላይ በተነሳው እሳት ተቀጣጣይ ነገር በጫኑ ሁለት ኮንቴነሮች ላይ እሳት መነሳቱ ተነግሯል

  • sheger1021fm
  • Apr 10
  • 1 min read

ትናንት ከጅቡቲ ተነስቶ የገቢ እቃዎችን ይዞ ወደ ሞጆ ይጓዝ በነበረ ባቡር ላይ በተነሳው እሳት ተቀጣጣይ ነገር በጫኑ ሁለት ኮንቴነሮች ላይ እሳት መነሳቱ ተነግሯል፡፡


በሶማሌ ክልል ቢኬ ባቡር ጣቢያ ላይ በደረሰው #የእሳት_አደጋ የሞተር ዘይት ጭነው ነበር ከተባሉት ሁለት ኮንቴነሮች አንደኛው በከፊል ተቃጥሏል ሁለተኛው ተርፏል ተብሏል፡፡


የሞተር ዘይት በጫነ ኮንቴይነር ላይ የተነሳው የእሳት አደጋ ምክንያት ገና እየተጣራ መሆኑን የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ተናግሯል፡፡


የእሳት አደጋው የደረሰው ሚያዝያ 1 ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ ከጅቡቲ ወደ ሞጆ በሚጓዝ የባቡር ፉርጎ ላይ በተጫነ ኮንቴነር ሲሆን የእሳት አደጋው የተከሰተበት ኮንቴነርም የሞተር ዘይት የጫነ ነበር ተብሏል፡፡

የኢትዮ ጅቡቲ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ የሆኑት ወይዘሮ እስራኤል ወልደመስቀል በሁለት ኮንቴነሮች የእሳት ቃጠሎው ተከስቶ ነበር ይላሉ፡፡


በባቡሩ ላይ ከተጫነው 26 ኮንቴነር መካከል አደጋው የደረሰው በ2ቱ ላይ ሲሆን አንድኛው ኮንቴር የበለጠ የእሳት ቃጠሎ እንደደረሰበት ነግረውናል፡፡


ጉዳት የደረሰባቸው ሁለቱም ኮንቴነሮች ጭነው የነበሩት #የሞተር_ዘይት ነበር ያሉን ወይዘሮ እስራኤል የደረሰው ጉዳት በገንዘብ ምን ያህል ነው የሚለው ለማወቅ ገና የማጣራት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡


የኢትዮጵያ የገቢና ወጪ እቃዎችን በማጓጓዥ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር አደጋውን በቁጥጥር ስር ለማዋል 3 ሰዓትን እንደወሰደ ጠቅሷል፡፡


ተመሳሳይ አደጋ እንዳይከሰትና ምን አልባትም ከዚህ በኋላ ቢከሰት ተቋሙ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ የሆኑት ወይዘሮ እስራኤል ወልደመስቀል ተናግረዋል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://www.mixcloud.com/ShegerFM/hjuykhyu/


በረከት አካሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page