ሚያዝያ 2 2017 - ማባሪያ ያላገኘው ግጭት ተንቀሳቅሶ ለመስራት አስቸጋሪ በመሆኑ ጋዜጠኞች የሞያ ግዴታቸውን እንዳይወጡ እንቅፋት ሆኗል ተባለ
- sheger1021fm
- Apr 10
- 1 min read
በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ማባሪያ ያላገኘው ግጭት ተንቀሳቅሶ ለመስራት አስቸጋሪ በመሆኑ ጋዜጠኞች የሞያ ግዴታቸውን እንዳይወጡ እንቅፋት ሆኗል ተባለ፡፡
ግጭቶች የመገናኛ ብዙሃን ጎራ እንዲይዙ ማድረጋቸውና ጋዜጠኞችም መረጃ እንዳያገኙ፣ በነፃነት የመናገር መብትም አደጋ ላይ እንዲወድቅ ምክንያት መሆኑን የዘርፉ ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡
በማህበረሰብ ውስጥ ያሉ ቁርሾዎች፣ የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ ሌላም ሌላም ተጨምሮ በነፃነት የመናገር መብት ላይ ክፉ ጥላ ማጥላቱን እንዲሁ፡፡
የሀገሪቱ የገጠማት የጂኦ ፖለቲካ ጉዳይ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያሉ አለመግባባቶች በአማራ እና በኦሮሚያ በትግራይ ክልል ያሉ ወታደራዊ ግጭቶችም የሚዲያውን በነፃነት የመናገር መብት አፍኖታል ብለዋል በጉዳዩ ያነጋገርናቸው የዘርፉ ባለሙያ፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
📌Spotify : https://shorturl.at/QG8f2
Comments