top of page

ሚያዝያ 2፣2016 - የኦሮሞ ነጻነት ግንባር(ኦነግ) የበቴ ኡርጌሳ ግድያ እንዲጣራለት ጠየቀ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር(ኦነግ) የበቴ ኡርጌሳ ግድያ እንዲጣራለት ጠየቀ፡፡


የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የፖለቲካ ኦፊሰር የሆኑት አቶ በቴ ኡርጌሳ ጭካኔ የተሞላበት ግድያ እንደተፈጸመባቸው ፓርቲው ባወጣው መግለጫ ተናግሯል፡፡


የፓርቲዉ የፖለቲካ ኦፊሰር በቴ አርጌሳ የተገደሉት ተወልደው ባደጉበት መቂ ከተማ እንደሆነ ኦነግ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስረድቷል፡፡


ኦነግ በግድያው ላይ ተጨማሪ ምርመራውን እያደረገ መሆኑን ተናግሮ፤ ሁኔታው ለሁላችንም በጣም ከባድ ነውም ብሏል በመግለጫዉ፡፡

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር(ኦነግ) በመግለጫዉ ሁሉም የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ሰላም ወዳድ ህዝቦች አፋጣኝ እና ገለልተኛ ምርመራ እንዲያደርጉ እንጠይቃለን ብሏል።


የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዳኒኤል በቀለ በበኩላቸዉ የበቴ ኡርጌሳን ግድያ በተመለከተ በኤክስ ገጻቸዉ ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ ፈጣን እና አድሎ የሌለበት ምርመራ እንዲደረግ ጠይቀው የክልሉ እና የፌደራል መንግስትም አጥፊዎችን ለህግ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Telegram: @ShegerFMRadio102_1



תגובות


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page