top of page

ሚያዝያ  18፣2016 - አንድ ሰው ብቻ በቅጡ መናገር የሚችለው ቋንቋ ኢትዮጵያ ውስጥ አለ ተባለ

አንድ ሰው ብቻ በቅጡ መናገር የሚችለው ቋንቋ ኢትዮጵያ ውስጥ አለ ተባለ፡፡


አንድ ሰው ብቻ በትክክል የሚናገረው ቋንቋ የብራይሌ ማህበረሰብ  ቋንቋ የሆነው አንጎታ ቋንቋ ነው ተብሏል።


የብራይሌ ማህበረሰብ አንጎታ ቋንቋን የሚናገሩ አምስት ሰዎች አሉ ቢባልም ቋንቋውን በቅጡ የሚያውቀው አንድ ሰው ብቻ መሆኑን የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ዲኤታ ወርቅነሽ ብሩ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ሲናገሩ ሰምተናል፡፡


ከ 145 አመታት በፊት የብራይሌ ብሔረሰብ ብዛት  8 ሺህ ያህል እንደነበረ ጥናት አሳይቷል ተብሏል፡፡


በአሁኑ  ሰዓት ግን ያሉት የብሄሩ ተወላጆችም ሆነ ቋንቋውን መናገር የሚችሉት አምስት ሰዎች ብቻ መሆናቸው ተነግሯል፡፡


በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የመጥፋት አደጋ የተጋረጠባቸው ሁለት ቋንቋዎች ከመጥፋት ለመታደግ ጥናት እና ምርምር እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡


ከብራይሌ በተጨማሪ ከፍተኛ የመጥፋት አደጋ ተጋርጦበታል የተባለው ሌላኛው ቋንቋ የባጫ ብሔረሰብ ቋንቋ የሆነው ባጫ ቋንቋ ነው ሲባል ሰምተናል፡፡


እነዚህን ቋንቋዎች ከመጥፋት ለመታደግ ከጂንካ እና ከአርባምንጭ ዩኒቨርስቲዎች ጋር በመሆን እየተሰራ እንደሆነ የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ወርቅነሽ ብሩ ተናግረዋል፡፡


በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት 57 ቋንቋዎች ስርዓተ ትምህርት ተቀርፆላቸው መማሪያ መሆናቸውን ሚኒስትር ዲኤታዋ አስረድተዋል፡፡


ንጋቱ ሙሉ/ማንያዘዋል ጌታሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Telegram:  @ShegerFMRadio102_1




Comments


bottom of page