ሚያዝያ 17 2017 - የኢትዮ ቴሌኮምን 10 በመቶ የሀብት ድርሻ ለህዝብ ለመሸጥ ባቀረበው የአክሲዮን ሽያጭ እስካሁን ከ47,000 በላይ ዜጎች አክሲዮን ገዝተዋል ተባለ
- sheger1021fm
- Apr 25
- 1 min read
የኢትዮ ቴሌኮምን 10 በመቶ የሀብት ድርሻ ለህዝብ ለመሸጥ ባቀረበው የአክሲዮን ሽያጭ እስካሁን ከ47,000 በላይ ዜጎች አክሲዮን ገዝተዋል ተባለ፡፡
10.7 ሚሊዮን አክሲዮን በመሸጥ እስካሁን 3.2 ቢሊዮን ብር ሰብስቢያለሁ ብሏል ተቋሙ፡፡
ይህም ለመሸጥ ያሰበውን 10 በመቶ አክሲዮን ብቻ ነው የሸጠው እንደማት ነው፡፡ ለሽያጭ የቀረበው አክሲዮን መጠን 100 ሚሊዮን እንደነበር ይታወሳል፡፡
በመጀመሪያው ዙር መደበኛ የአክሲዮን ሽያጭ ከቀረበው 100 ሚሊዮን አክሲዮን ውስጥ ዝቅተኛ ሽያጭ 33 ድርሻ በገንዘብ 9,900 ብር ብቻ መሆኑንና ከፍተኛው ደግሞ 3333 ወይም 999,900 ብር መሆኑ መነገሩ ይታወሳል፡፡

የአንድ አክሲዮን ሽያጭም 300 ብር እንደነበርም አይዘነጋም፡፡
ቀሪ አክሲዮኖችን በተመለከተ ዝርዝር የሽያጭ ሂደቱን በመጪው ጊዜ አሳውቃለሁ ሲል ኢትዮ ቴሌኮም በመግለጫው ተናግሯል፡፡
አክሲዮን የገዙ ባለ ድርሻዎችን መብት ባስጠበቀ መልኩ እንዲሁም ጉዳዩ የሚያገባቸው ይሁንታ በማግኘትም በድጋሚ ለገበያ የሚቀርብ መሆኑን እወቁልኝ ብሏል፡፡
ትዕግስት ዘሪሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
Comments