top of page

ሚያዝያ 16 2017 - ‘’የገቢዎች ቢሮ ከአቅም በላይ የሆነ ግብር ጥሎብናል’’ የአዲስ አበባ ልኳንዳ ነጋዴዎች ማህበር

  • sheger1021fm
  • Apr 24
  • 1 min read

‘’የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በልኳንዳ ቤቶች ላይ ከአቅም በላይ የሆነ ግብር ጥሎብናል’’ ሲል የአዲስ አበባ ልኳንዳ ነጋዴዎች ማህበር ቅሬታውን አሰማ፡፡


አቤቱታውን ለከንቲባ ፅህፈት ቤት በደብዳቤ ቢያሰማም ምላሽ እንዳላገኘ ማህበሩ ነግሮናል፡፡


የአዲስ አበባ ልኳንዳ ነጋዴዎች ማህበር ምን አለ?


የሚጠበቅባቸውን #ግብር እየከፈሉ አይደለም በሚል አሁን እንድንከፍል የተደረገው የገቢ ግብር ከአቅማችን በላይ የሆነነ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ልኳንዳ ነጋዴዎች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ አየለ ሳህሌ ነግረውናል፡፡


እርሳቸው እንደሚሉት የቁም እንሰሳቱን ግዚን በተመለከተ ለቢሮው የምናቀርበው ደረሰኝ ተቀባይነት አይገኝም ይቀረባችሁት ደረሰኝ ህገወጥ ነው እንባላለን፤ የቁም እንሰሳት ነጋዴውን ሲስተሙ አያውቀውም እየተባለ እዳው ሁሉ እኛ ላይ እየተጫነብን ነው ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡


ቅሬታ አቅራቢዎቹ እንደሚሉት የቁም እንሰሳት ነጋዴዎቹ ደረሰኝ እንዲቆርጡ ማድረግ ሲገባ ይህ ባለመደረጉ በቁም እንሰሳት ግብይት ወቅት በአደባባይ ህገወጥ ደረሰኝ የሚነግዱ ሰዎች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆኗል፡፡


የልኳንዳ ነጋዴዎቹ የተጣለባቸውን ግብር ከከፈሉ በሁዋላ የቢሮው ሰራተኛ ነን የሚሉ ግለሰቦች የመሸጫ ቦታቸው ድረስ እየመጡ ከደረሰኝ ጋር አያይዘው የእጅ እንዲሰጧቸው የሚያስጨመንቋቸው አሉ ብለዋል፡፡


የገጠሙንን ችግሮች በሙሉ በደብዳቤ አስፍረን ለከንቲባ ፅህፈት ቤት ቅሬታችንን ካሰማን አመትሊሆነን ነው እስካሁን መፍትሄ አላገኘንም ብለውናል አቶ አየለ፡፡


የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በ9 ወራት ሪፖርቱ ልኳንዳ ቤቶችን ጨምሮ ሌሎችንም ወደ ቫት ስርዓቱ በማስገባት የሚጠበቅባቸውን እንዲከፍሉ እያደረገ መሆኑንና ደምበኞቹን ሳያስጨንቅ ግብሩን እንደሰበሰበ ጠቅሷል፡፡


በማህበሩ የቀረቡ ጥያቄዎችን ይዘን ማብራሪያ እንዲሰጠን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮን ለመጠየቅ ያደረግነው ጥረት ለጊዜው ሃላፊዎቹን ባለማግኘታችን አልተሳካም የልኳንዳ ነጋዴዎቹ ላነሱት ጥያቄ የቢሮውን መልስ እንዳገኘን ይዘን እንመለሳለን፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….



ምንታምር ፀጋው

Comentarios


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page