top of page

ሚያዝያ 16 2017 - ተማሪዎች ከ2018 ጀምሮ ት/ቤት ስልክ ይዘው እንዳይገቡ ይደረጋል መባሉ ት/ቤቶችና መምህራን እንዴት ያዩታል?

  • sheger1021fm
  • Apr 24
  • 1 min read

ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎች ከ2018 ጀምሮ ትምህርት ቤት ውስጥ #ስልክ ይዘው እንዳይገቡ የሚያደርግ ህግ ሊተገብር ማቀዱን ተናግሯል፡፡


ህጉን ወደ መሬት ለማውረድ ትምህርት ሚኒስቴር ከዘርፉ አመራሮች ጋር፤ እንደ ሀገር ወጥ የሆነ መግባባት ላይ ለመድረስ ውይይት ለማድረግ እቅድ መያዙን ሰምተናል፡፡


ታዲያ ህጉ ትምህርት ቤቶች እንዴት ያዩታል? መምህራን በዚህ ዙሪያ ምን ሃሳብ አላቸው ብለን ጠይቀናል፡፡


ተማሪዎች አሁን ላይ ክፍል ውስጥ ስልክ ይዘው ሲማሩ ‘’ትምህርት ከመከታተል ይልቅ ማህበራዊ ትስስር ገፅ ነው የሚጠቀሙት’’ የሚሉ እንዳሉ ሁሉ ‘’የመፅሀፍት እጥረትን ተከትሎ አንዳንድ ተማሪዎች ስልካቸውን በመጠቀም የተለያዩ አጋዥ መፅሀፍትን ከተለያዩ ድህረ ገፆች በማውረድ የሚያነቡ አሉ’’ የሚል ሀሳብ ያላቸውም አሉ፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….


በረከት አካሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…






Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page