top of page

ሚያዝያ 16 2017 - መሰረቱን በህንድ ያደረገው ቫይደም የተሰኘው የህክምና አማካሪ ተቋም በኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ከፈትኩ አለ

  • sheger1021fm
  • Apr 24
  • 1 min read

መሰረቱን በህንድ ያደረገው ቫይደም (Vaidam Health) የተሰኘው የህክምና አማካሪ ተቋም በኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ከፈትኩ አለ፡፡


እንደ ኩላሊት፣ የመቅኔ ንቅለ ተከላ እና ሌሎች ከኢትዮጵያ ውጭ የሚደረጉ ህክምናዎችን የማማካር እና የጉዞ ሂደትን ማመቻቸት ላይ ትኩረት አድርጌ እሰራለሁ ብሏል፡፡


ወደ ውጭ ሀገር ለህክምና ለመውጣት ሲታሰብ የት ሀገር፣ የትኛው ሆስፒታል ልታከም እና ሌሎችም ለታማሚውም ሆነ ለአስታማሚው ቤተሰብ አሳሳቢ ጉዳይ ነው ያለው የቫይደም ሄልዝ ሜዲካል ኮንሰልተንሲ ሰርቪስ በተለይ አጣዳፊ የህክምና ጉዞ ከሆነ ሊያጋጥማቸው የሚችለው ችግር ቀላል አይደለም ብሏል።


ለዚህ ደግሞ ድርጅቱ በኢትዮጵያ ቢሮ መክፈቱ ጥቅሙ ቀላል የሚባል አይደለም የተባለ ሲሆን ታካሚው ትክክለኛ ሀኪም እና ሆስፒታል እንዲያገኝ ያግዛል ተብሏል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….

ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…






Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page