top of page

ሚያዝያ 16 2017 - ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ በቀን እስከ 15,000 ቶን (150,000 ኩንታል) ሲሚንቶን እያመረትኩ ነው አለ

  • sheger1021fm
  • Apr 24
  • 1 min read

ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ በቀን እስከ 15,000 ቶን (150,000 ኩንታል) ሲሚንቶን እያመረትኩ ነው አለ፡፡


ይህም በአጭር ጊዜ ውስጥ የሲሚንቶ ገበያ እንዲረገጋ አድርጓል ብሏል፡፡


ፋብሪካው ባለፉት 6 ወራት ከ12 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ሲሚንቶ ወደ ገበያ ማቅረቡንም ተነግሯል፡፡


ፋብሪካውም በሙሉ አቅም ወደ ምርት ሂደት የገባው በያዝነው ዓመት መስከረም ወር ላይ እንደሆነ ይታወሳል።


ባለፉት 6 ወራት በሲሚንቶ ገበያው ላይ ከፍተኛ መረጋጋትና የዋጋ ቅናሽ ከማሳየት ባለፈም ሲሚንቶን ለማግኘት በየፋብሪካው ይኖር የነበረውን ወረፋ ሙሉ ለሙሉ አስቀርቻለሁ ብሏል።

ፋብሪካው ከኢትዮጵያ የሲሚንቶ ገበያ ውስጥ ከ38 በመቶ በላይ የሚሆነውን የሲሚንቶ አቅርቦት ሸፍኛለሁ ሲልም አስረድቷል፡፡


በአማራ ክልል በእንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ አቅራቢያ የተገነባው ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ በሚገኝበት አካባቢ የምገባ ማእከል፣ የተማሪዎች ድጋፍና የቤት ማደስ ስራዎችን እና መሰል ስራዎችን እየከወነ መሆኑንም ሰምተናል፡፡


ፋብሪካው ወደፊት ከሲሚንቶ በተጨማሪ ለአፈር ማገገም ከፍተኛ ሚና ባለው የጂብሠም ምርት ዘርፍ ለመሠማራት የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝም ተናግሯል፡፡


ፍቅሩ አምባቸው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…






Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page