መንግስት ከዶላር አንፃር የብርን የመግዛት አቅም ሊያዳክም እንደሚችል ከምናልባትም በላይ የሆኑ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡
ይህም ከአለም የገንዘብ ድርጅት ብድር ለማግኘት የተቀመጠላት ቅድመ ሁኔታ እንደሆነ ይነገራል፡፡
በብዛት ምርቶችን በዶላር ከውጭ ገዝታ የምታስገባው ኢትዮጵያ፤ ከዚህ በላይ የብርን የመግዛት አቅም ብታዳክም የኑሮ ውድነቱን እንደሚያባብሰው የምጣኔ ሐብት ባለሞያዎች ስጋት አለን እያሉ ነው፡፡
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም የወሰደችው ብድር ለመክፈልም እንደምትቸገር ይጠቅሳሉ፡፡
ታዲያ መላው ምንድን ነው?
ንጋቱ ረጋሣ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: @ShegerFMRadio102_1
Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments