top of page

ሚያዝያ 10፣2016 - ኢትዮጵያ ለማምረቻ ማሽነሪዎች መግዣ በየዓመቱ 1.3 ቢሊዮን ብር ወጪ ታደርጋለች ተባለ

ኢትዮጵያ ለማምረቻ ማሽነሪዎች መግዣ በየዓመቱ 1.3 ቢሊዮን ብር ወጪ ታደርጋለች ተባለ።

ከእነዚህ ማሽነሪዎች 91 በመቶዎቹ ከውጪ የሚገዙ እንደሆኑ ተነግሯል።

‘’የካፒታል ዕቃ ሊዝ ፋይናንስ’’ ለአምራች ኢንተርፕራይዞች ማሽነሪ በብድር የሚቀርብበት ስርአት ነው።


አምራች ኢንተርፕራይዞቹ ደግሞ ቀስ በቀስ ብድሩን ከፍለው በመጨረስ ማሽኑን የራሳቸው ያደርጉታል።


በብድር ለሚቀርቡት ማሽኖች መግዣ የሚያስፈልገውን ገንዘብ በዋናነት የሚያቀርበው፤ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሲሆን ራሱን የቻለ ፕሮጀክትም እንዳለው ተነግሯል።


ፕሮጀክቱ ከአለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የማምረቻ ማሽነሪዎችን ገዝቶ የሚያቀርብ ነው ሲሉ፤ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ አሸናፊ መለሰ ነግረውናል።


በኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና በፕሮጀክቱ አማካይነት ባለፉት ጥቂት አመታት ከ32 ሺህ የሚበልጡ የማምረቻ ማሽነሪዎች፤ ለኢንተርፕራይዞች ቀርበዋል ያሉን አቶ አሸናፊ ግምታዊ ዋጋቸውም ወደ አስራ ስድስት ቢሊየን ብር እንደሆነ አክለዋል።


ኢትዮጵያ በአጠቃላይ ወደ 1.3 ቢሊየን ብር የማምረቻ ማሽነሪዎችን ለመግዛት እንደምታወጣ የተናገሩት ስራ አስፈጻሚው፤ ከእነዚህ ውስጥ 91 በመቶዎቹ ከውጪ የሚገቡ ናቸው ብለዋል።

በሀገር ውስጥም ግን እነዚህን ማሽነሪዎች የሚያመረቱ ፋብሪካዎች ያሉ ሲሆን፤ ማሽነሪዎችን ከእነሱ በመግዛት በብድር ማቅረብ ቢቻል በብዙ ማትረፍ ይቻላል ብለውናል።


በዚሁ ጉዳይ ላይ ከሠሞኑ ከሀገር ውስጥ ማሽነሪ አምራቾች ጋር ውይይት መካሄዱንም ነግረውናል።


ከሀገር ውስጥ አምራቾች ማሽኖቹን መግዛት በኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና በካፒታል ዕቃ ሊዝ ፋይናንስ፤ አክስዮን ማህበራት በኩል የሚነሱ ችግሮችንም እንደሚያስቀር አቶ አሸናፊ ተናግረዋል።

የሀገር ውስጥ ማሽነሪ አምራቾች አቅም እንዲያድግ መርዳት በአለም አቀፍ ገበያም ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ያግዛል ተብሏል።



ንጋቱ ረጋሣ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Telegram: @ShegerFMRadio102_1




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page