ሚያዝያ 1 2017 - የኤሌክትሪክ አገልግሎት ካለፉት 3 ቀናት ጀምሮ በሲስተም መቋረጥ ምክንያት ደንበኞች ሒሳብ እየከፈሉን አይደለም አለ
- sheger1021fm
- Apr 9
- 1 min read
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ካለፉት ሶሰት ቀናት ጀምሮ በሲስተም መቋረጥ ምክንያት ደንበኞች ሒሳብ እየከፈሉን አይደለም አለ፡፡
ቴክኒካል ያለውን ችግር ለመፍታት እየሰራ መሆኑን የተናገረው አገልግሎቱ የመክፈያ የጊዜው ገደቡ ቢያልፍ እንኳን የደንበኞችን አገልግሎት አናቋርጥም ወይም ቆጣሪ አንቆርጥም ሲል ተናግሯል፡፡

አገልግሎቱ በባንክ ሒሳብ የሚከፈልበት ሲስተም ብቻ ሳይሆን የክፍያ መረጃን ጨምሮ ቅሬታ ፣ ጥቆማና ጥያቄዎችን የሚቀበልበት 905 እና 904 ነፃ የጥሪ ማዕከሎችም እንደማይሰሩ ተነግሯል፡፡
ተቋሙ ለተፈጠረው የአገልግሎት መስተጓጎል ይቅርታ ጠይቆ በተቻለ ፍጥነት ሲስተሙ ያጋጠመውን ችግር ለመፍታት እና አገልግሎት ለማስጀመር እየሰራሁ በመሆኑ በትዕግስት ጠብቁን ብላችኋል፡፡
ትዕግስት ዘሪሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
📌Spotify : https://shorturl.at/QG8f2
Kommentit