ሚያዝያ 1 2017 - ኢትዮ ቴሌኮም ከ14,000 በላይ የኤሌክተእሪክ መኪኖችን የኤሌክትሪክ ሀይል ቻርጅ አድርጌያለሁ አለ።
- sheger1021fm
- Apr 9
- 1 min read
ኢትዮ ቴሌኮም በ2 ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ ባስገባሁት እጅግ ፈጣን የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ ጣቢያ ከ14,000 በላይ የኤሌክተእሪክ መኪኖችን የኤሌክትሪክ ሀይል ቻርጅ አድርጌያለሁ አለ።
ይህ ማለትም በአለም አቀፍ አካባቢ ሳይንስ ጥበቃ መሰረት 2,622 ዛፎችን እንደመትከል ነው ተብሏል።
ኩባንያው ይህን የተናገረው ዛሬ በተጨማሪ 16 መኪኖችን በተመሳሳይ ሰአት ቻርጅ የሚደረግበት ጣቢያ ገንብቶ ለህዝብ ክፍት ባደረገበት ጊዜ ነው።
ኢትዮ ቴሌኮም የገነባውን ሁለተኛውን እጅግ ፈጣን የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ ጣቢያ ከመገናኛ ወደ ቦሌ መስመር በቀኝ በኩል አንበሳ ጋራዥ ፊት ለፊት ታገኙታላችሁ ተብላችኃል።
ኩባንያው በተለይ ሀገር ለነዳጅ የምታወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ለማትረፍ እና ለህዝብ እጅግ በቅናሽ ዋጋ ነው አቀርብኩት ያለውን አገልግሎት በቴክኖሎጂ ለመደገፍ በብርቱ እየሰራ መሆኑን የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።

ሁለተኛው እጅግ ፈጣን የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ ጣቢያ ከዛሬ ጀምሮ 24 በ7 ለደንበኞች ክፍት መሆኑ ተሰምቷል።
በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መስፋፋት ጋር ተያይዞ ወደ አገልግሎት የገባው ኤሌክትሪክ መኪና መሙያ ጣቢያ በየጊዜው እያደገ የመጣውን ፈጣንና ቀልጣፋ የኃይል መሙያ ሶሉሽኖችን ፍላጎት ለማሟላት የሚደረገውን ጥረት በብርቱ ይደግፋል ተብሏል።
ከዚህ ቀደም ኩባንያው ከቦሌ ወደመገናኛ በሚወስደው አውራጎዳና ላይ 16 መኪኖችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚችል የኤሌክትሪክ መኪና መሙያዎችን የያዘ ጣቢያ ገንብቶ ወደስራ ማስገባቱ ይታወቃል፡፡
በዚህ አገልግሎትም ለ14,280 የኤሌክትሪክ መኪኖች አገልግሎት አግኝተዋል።
ለዚህም አገልግሎት 376,574.72 ኪሎዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ጥቅም ላይ ውሏል ተብሏል።
ይህ በመሆኑም 521,074.23 ኪሎ ግራም ካርቦንዳይ ኦክሳይድ ወደ ከባቢ አየር እንዳይለቀቅ መከላከል እንደተቻለ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አስረድተዋል።
ተህቦ ንጉሴ
Comments