top of page

ሚያዝያ 1፣2016 - የውጭ ምንዛሪ ምንጭ የሆነው ቡና፤ ግብይቱ ቀደም ባሉ ዓመታት የሚካሄደው በምርት ገበያ በኩል ብቻ ነበር

የኢትዮጵያ ዋነኛ የውጭ ምንዛሪ ምንጭ የሆነው ቡና፤ ግብይቱ ቀደም ባሉ ዓመታት የሚካሄደው በኢትዮጵያ ምርት ገበያ በኩል ብቻ ነበር።


ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ ግን ግብይቱ ከምርት ገበያው ውጪም እንዲከናወን ተፈቅዷል።


ይሄ የተለያዩ ችግሮችን አስከትሏል የሚለው የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ውሳኔው ዳግም ሊታይ ይገባል ባይም ነው።


የምርት ገበያው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወንድማገኘሁ ነገራ፤ ከ2013 ጀምሮ በኢትዮጵያ ምርት ገበያ በኩል በሚካሄድ የቡና ግብይት ላይ የዋጋ ገደብ እንዲቀመጥ መደረጉን የተናገሩ ሲሆን ይህም አምራች አርሶ አደሮችን ለመጠበቅ በማሰብ የተደረገ ነው ብለዋል።


የቡና ዋጋ በምርት ገበያው ተገድቦ በሌሎች አማራጮች ግን ይህ ገደብ ባለመኖሩ በምርት ገበያው በኩል

የሚደረገው የምርቱ ግብይት እየቀነሰ መምጣቱን አቶ ወንድማገኘሁ ተናግረዋል።


የቡና ግብይት ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ውጪም እንዲካሄድ መፈቀድ ብድር ለታለመለት አላማ ብቻ መዋሉን ፤

የማረጋገጡን ስራን አስቸጋሪ አድርጎታል ሲሉ ዋና ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡


ሻጮች ገንዘባቸውን ያለ ስጋት ያገኙ የነበረበትን አሰራርም ቀይሮየታል ብለዋል።


የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን በበኩሉ በቀጥታ የግብይት አማራጭ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን በመለየት መፍትሔ ለመስጠት እየሰራሁ ነው ብሏል።


ንጋቱ ረጋሣ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Telegram: @ShegerFMRadio102_1



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page