top of page

ሚያዝያ 1፣2016 - በኢትዮጵያ አሁን ላይ 56 የህፃናት የቀዶ ህክምና ባለሞያዎች ብቻ መኖራቸው ሰምተናል

በኢትዮጵያ የሕፃናት ህክምና አገልግሎት፤ አንድ የህፃናት የቀዶ ህክምና ባለሞያ ለአንድ ሚሊዮን ህፃናት እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡


በዚህ ላይ ህብረተሰቡ ስለህክምናው ያለው ግንዛቤ እጅግ አነስተኛ ነው ተብሏል፡፡


በኢትዮጵያ አሁን ላይ 56 የህፃናት የቀዶ ህክምና ባለሞያዎች ብቻ መኖራቸው ሰምተናል፡፡


በመንግስትም በኩል ቢሆን ለእነዚህ በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሰራሽ አደጋ የቀዶ ህክምና ለሚያስፈልጋቸው ህፃናት እራሱን የቻለ ሆስፒታልም ሆነ የጤና ተቋም መገንባት አልተቻለም፡፡


ይህ ደግሞ ህፃናቱ ለሚያስፈልጋቸው የቀዶ ህክምና አገልግሎት የሚሰጠው ትኩረት ምንያህል አነስተኛ እንደሆነ ያሳያል ተብሏል፡፡


ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ይሰጥ የነበረው ቀዶ ህክምና፤ አሁን ላይ በ17 ሆስፒታሎችና በ7 ክልሎች እየተሰጠ እንደሆነ ተነግሯል፡፡


የአገልግሎቱ አሰጣጥ ሁሉም ጋር ተደራሽ ለማድረግ እና ያለውን የግንዛቤ ክፍተት ለማስተካከል ከመንግስትም ሆነ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ድጋፍ ያስፈልጋል ተብሏል፡፡


ማርታ በቀለ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Telegram: @ShegerFMRadio102_1



Commentaires


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page