መጋቢት 9 2017 - የኢትዮ - ጅቡቲ ምድር ባቡር እቃ ወደ ሀገር ቤት ለማስገባት ስራ መጀመሩን ተከትሎ ከቡና ላኪዎችና ከሚመለከታቸው ጥያቄ ቀረበበት
- sheger1021fm
- Mar 18
- 1 min read
የኢትዮ - ጅቡቲ ምድር ባቡር ከትራንስፖርት ባለፈ በአለም ግዙፍ ኢኮኖሚ በሚገላበጥበት የዕቃ ገቢና ወጭ ማስተላለፍ፣ የመርከብ ክሊራንስ፣ የጉምሩክ ማለፍያ ሰነድ አጠናቆ ከጅቡቲ ወይም ከመነሻ ሀገር እቃ ወደ ሀገር ቤት ለማስገባት ስራ መጀመሩን ተከትሎ ከቡና ላኪዎችና ከሚመለከታቸው ጥያቄ ቀረበበት።
ለአስመጭ ላኪዎች በውጭ ምንዛሪ የሚከፍሉት ቅጣትና የመጋዘን ኪራይ እንዲሁም ከገቢና ወጭ ንግድ መሀል ያለውን መዝረክረክ በብርቱ ያስቀራል የተባለው ይህ ስራ ገና ከመጀመሩ የቅልጥፍና ስጋት ተነስቶበታል።
የኢትዮጵያ ገቢና ወጭ ንግድ ያቀላጥፋል የተባለለት ጥልፍልፍ አሰራሮችንም ያስቀራል በሚል ተስፋ የተደረገበት ስርአት ዘርግቶ በዚያው መንገድ መጓዝ መጀመሩን የኢትዮ - ጅቡቲ ምድር ባቡር ተናግሯል።
#የኢትዮ_ጅቡቲ_ምድር ባቡር ይህንን ስጋት ሰምቶ ምላሽ ሰጥቷል።
የኢትዮ - ጅቡቲ ምድር ባቡር ዋና ስራ አስፈፃሚ ታከለ ኡማ ስራው በትብብር የሚሰራ እንጂ ምድር ባቡሩ ላይ ብቻ የሚጣል እንዳልሆነ በብርቱ ተናግረዋል።
ጨምረውም ነጋዴዎች የተዝረከረከ የዶክመንት አያያዛቸውን ጥንቅቅ አድርገው እንዲጨርሱ መክረዋል።
ይህ ሲሆን በኢትዮጵያ በግዙፍ ኢኮኖሚ በወጭና ንግድ ገቢ ንግድ ማዕዘን የኢትዮ - ጅቡቲ ምድር ባቡር የፍሬይትና የመልቲ ሞዳል አገልግሎት መስጠት በመጀመሩ ውጤት ይመጣል ተብሏል።
የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር የጠቅላላ ንግድ ሸቀጥ ገቢና ወጭ ዕቃ ከሚነሳበት ሀገር ከመርከብ ጀምሮ ከጅቡቲም ሀገር ያለውን የወረቀት ስራ የጉምሩክ መስመር አጠናቆ ወደ ሀገር ቤት ለማስገባት ወደ ውጭም ለመላክ ስራ መጀመሩ ታውቋል።
የኢትዮ - ጅቡቲ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በቅርቡ በጀመረው የመልቲ ሞዳል አገልግሎትን ተንተርሶ የቡና እንዲሁም አበባ ላኪዎች ምርቶቻቸውን ለመላክ ለኮርፖሬሽኑ ጥያቄ ማቅረባቸውም ተሰምቷል።
የመልቲ ሞዳል አሰራር ከዳር እስከ ዳር ጭነት ማጓጓዣ ጨምሮ ሁሉንም አገልግሎቶች ያካተተ ነው፡፡
ይህ ስራ በሎጅስቲክስ መዓዘን ያለውን የገቢና ወጪ ንግድ ራስ ምታት ያቀለዋል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ተህቦ ንጉሴ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
留言