በኢትዮጵያ ያሉ ግጭቶች በስራዬ ላይ እንቅፋት ሆነዋል ሲል የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተናገረ፡፡
በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ግጭቶች የምክክሩ ሂደት እንዲጓተት ምክንያት መሆናቸውን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ ተናግረዋል፡፡
‘’በሄድንበት ሁሉ የሰላም ጥማት አለ ያሉት ኮሚሽነሩ ይህም ስራችንን በአግባቡ እንዳንሰራ እንቅፋት ሆኗል’’ ሲሉ አስረድተዋል፡፡
‘’የምክክሩ ሂደት ዘግይቷል እየተባለ የሚነሳው ቅሬታም ልክ ነው ይህ እንዲሆን ያስቻለው ደግሞ የሰላም እጦቱ ነው’’ ማለታቸውን ሰምተናል፡፡
‘’ህዝቡ ሰላም ናፍቆናል ቶሎ ቶሎ በሉና ወደ ምክክሩ ግቡ ይለናል የሰላም እጦቱ ደግሞ ያን ለማድረግ አይፈቅድም’’ ብለዋል፡፡
ኮሚሽነር መስፍን ‘’አንዳንዶች የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተቋቋመ ወዲህ ነው ግጭት የበዛው ይላሉ፤ እውነቱ ግን ግጭቶቹ ከኛጋር ምንም አይነት ግንኙነት የላቸውም’’ ሲሉ አስረድተዋል፡፡
‘’የትጥቅ ትግል የመረጡትም፣ ጫካ የገቡትም፣ በሰላማዊ መንገድ እየታገሉ ያሉትም ሁሉም ለኛ ልጆቻችን ናቸው’’ ያሉት ኮሚሽነሩ ‘’በችግሮቻቸው ዙርያ አብረን እንድንመክር ተደጋጋሚ ጥሪ እያደረግን ነው’’ በለዋል፡፡
‘’ምክክሩ ልሂቃንም፣ ሃሳብ አመጭዎችም፣ ጉልበተኞችም፣ ጉልበት የሌላቸውም፣ እኩል ቁጭ ብለው የሚወያዩበት ስለሆነ የምክክሩን መንገድ መምረጥ ይበጃል’’ ብለዋል ዋና ኮሚሽነር መስፍን፡፡
‘’የሰላም እጦት ሁሉንም የህብረተሰብ ከፍል ነው የሚጎዳው ያሉት ኮሚሽነሩ የሚሞቱትም የሚገሉትም የኛው ልጆች ናቸው’’ ብለዋል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
תגובות