መጋቢት 8 2017 - ኤልሳቤጥ ወልደጊዮርጊስ(ዶ/ር) ከዚህ አለም በሞት ተለዩ
- sheger1021fm
- Mar 17
- 1 min read
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር በመሆን ያገለገሉት ኤልሳቤጥ ወልደጊዮርጊስ(ዶ/ር) ከዚህ አለም በሞት ተለዩ፡፡

በኮኔል ዩኒቨርሲቲ እና በኒውዮርክ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ትምህርታቸውን የተከታተሉት ዶ/ር ኤልሳቤጥ በሸገር ሬዲዮ በ #ሸገር_ካፌ ፕሮግራም በሥነ ጥበብና ታሪክ ጉዳዮች ላይ በተደጋጋሚ በመቅረብ እውቀታቸውን አካፍለዋል፡፡
ለስራ ከቆዩበት በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ሻርጃ ከተማ ማረፋቸው ተሰምቷል፡፡
የዶ/ር ኤልሳቤጥ አስከሬን ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ሰምተናል፡፡
ለዶ/ር ኤልሳቤጥ ወልደጊዮርጊስ ወዳጅ ዘመዶች ሸገር መፅናናትን ይመኛል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
ነብስ ይማር!