top of page

መጋቢት 8 2017 - አዋሽ ባንክ የረመዳን ወርን ምክንያት በማድረግ 23.5 ሚሊዮን ብር ለተለያዩ ተቋማት እና አቅመ ደካሞች  ድጋፍ አደረገ።

  • sheger1021fm
  • Mar 17
  • 1 min read

አዋሽ ባንክ የረመዳን ወርን ምክንያት በማድረግ 23.5 ሚሊዮን ብር ለተለያዩ ተቋማት እና አቅመ ደካሞች  ድጋፍ አደረገ።


ባንኩ 23.5 ሚሊዮን ብሩን የሰጠው ለአራት ተቋማት ነው።


በዚህም መሰረት ለ #አንዋር_መስጂድ የከርሰ ምድር ቁፋሮ የሚውል 7 ሚሊዮን ብር፣ በኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት ለሚያደርጉ 20 አቅመ ደከሞች 6.9 ሚሊዮን ብር፣ ለአወሊያ ዕርዳታ እና ልማት ድርጅት ትምህርት ቤት ማስፋፊያ 5 ሚሊዮን ብር እና በአሚን ጠቅላላ ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት ለሚያደርጉ 12 ታማሚዎች 4.6 ሚሊዮን ብር ተሰጥቷቸዋል።


አዋሽ ባንክ በዛሬው እለት በሸራተን ሆቴል ለእስልምና እምነት ተከታይ ደንበኞቹ ባዘጋጀው የኢፍጠር መርሃ ግብር ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ'ን ጨምሮ የባንኩ ደንበኞች ተገኝተዋል።


የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው ባንኩ ከ 983 በላይ ቅርንጫፎቹ በመስኮት ደረጃ ከሚሰጠው ከወለድ ነፃ የባባንክ አገልግሎት በተጨማሪ ከ50 በላይ  ሙለ በሙለ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በሚሰጡ ቅርንጫፎች ከ2.7 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን  እያስተናገደ መሆኑን አስረድተዋል።

በዚሁ መንገድም ከ28.2 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ መሰብሰቡን ጠቅሰዋል።


በተለያዩ የንግድ ዘርፍ ለተሰማሩ ከወለድ ነፃ ደንበኞችም ከ12.2 ቢሊዮን ብር በላይ የፋይናንሲንግ አገልግሎት መሰጠቱን ዋና ስራ አስፈፃሚው ተናግረዋል።


ባንኩ የ1446ኛውን የ #ረመዳን ወርን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ እና በዘጠኝ የክልል ከተሞች በተመረጡ 41 ከተሞች ውስጥ ከሁለት ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸዉ እና አቅመ ደካማ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍል የገንዘብ እና የዓይነት ድጋፍ ማድረጉም ተነግሯል።


ንጋቱ ሙሉ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page