መጋቢት 8 2017 - ሙዚቀኛ መርዓዊ ስጦት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
- Mar 17, 2025
- 1 min read
በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር ከ60 ዓመታት በላይ በተለይ በክላርኔት ጨዋታ የሚታወቁት ሙዚቀኛ መርዓዊ ስጦት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡
ከሙዚቀኞች ማህበር እና ከቤተሰቦቻቸው እንደሰማነው ሙዚቀኛው በህመም ምክንያት በተወለዱ በ90 ዓመታቸው ትናንት አመሻሽ 12 ሰዓት ገደማ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
መርዓዊ ስጦት ከክላርኔ መጫወት ባለፈ የግጥምና ዜማ ደራሲነት እና አቀናባሪነት የሚታወቁ እንደነበሩ ሙዚቀኛ ዳዊት ይፍሩ ነግረውናል፡፡
ሙዚቀኛ መራዊ 1928 ዓ.ም በደቡብ ወሎ ዞን በአምባሰል ወረዳ እንደተወለዱ የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል፡፡
ሙዚቀኛሙዚቀኛ መርዓዊ ስጦት በሞያቸው በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ የተለያዩ ሽልማቶች አግኝተዋል፡፡
ወንድሙ ሀይሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r





Comments