top of page

መጋቢት 6፣2016 - ሰዋሰዉ መልቲሚዲያ እና ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አብረን እንስራ ተባባሉ

  • sheger1021fm
  • Mar 15, 2024
  • 1 min read

ስመምነቱ በሙዚቃ አልበሞች እና በሁነት ዝግጅቶች በጋራ ለመስራት ነው ተብሏል።

 

ሁለቱ ኩባንያዎች ይህንኑ ለመስራት በዛሬው እለት ተፈራርመዋል።

 

ከሰዋሰዉ ጋር ከሚሰሩ ድምፃዉያን መካከል አንዱ የሆነዉ እና ከፋሲካ ፆም በኋላ የሚለቀቀዉን የአማኑኤል ሙሴ አልበም፤ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የስፖንሰርሺፕ ድርሻዉን መዉሰዱ በዛሬዉ እለት ይፋ ተደርጓል ተብሏል።

 

‘’ጥቁር ዉሃ’’የተሰኘዉ አልበሙም በሳፋሪኮም አጋርነት በሰዋሰዉ መተግበሪያ እንደሚለቀቅ ተነግሯል።

 

በስመምነቱ መሰረት ድምፃዊያን በመልቲሚዲያው በኩል ለአልበማቸዉ ከሚያገኙት ገንዘብ በተጨማሪ ከስፖንሰር አድራጊዉ ካምፓኒም ክፍያ እና ልዩ የሆኑ ጥቅማ ጥቅሞችን ያገኛሉ ተብሏል።

 



የሰዋሰዉ መልቲሚዲያ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሀብቱ ነጋሽ "ድምፃዊያን የድካማቸዉን ዋጋ እንዲያገኙ ከዚህም በላይ መስራት ይጠበቅብናል ያሉ ሲሆን፤ እንደ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ያሉ ግዙፍ ካምፓኒዎች ወደ ሀገራችን የሙዚቃ ኢንዱስትሪ መቀላቀላቸዉ ዘርፉን በሚገባ እንደሚደግፈዉም" አንስተዋል።

 

የኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ የተቀላቀለው ሰዋሰው  መልቲሚዲያ ከአንድ መቶ በላይ አንጋፋና ወጣት ድምፃዊያንን እና ሙዚቀኞችን በማስፈረም እየሰራ ይገኛል።

 

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዲጁታል ኢትዮጵያን ለመገንባት፤ በሀገሪቱ ውስጥ ጥራት ያለው የቴሌኮም አገልግሎት እንዲሰፋ ለማድረግ በኢትዮጵያ የግል የቴሌኮም አቅራቢ ሆኖ እየሰራ ይገኛል።

 

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

 

 

Комментарии


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page