top of page

መጋቢት 6፣2016 - መንግስት የሚወስዳቸው ብድሮች እዳቸው ለትውልድ እንዳይተላለፍ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ተጠየቀ

  • sheger1021fm
  • Mar 15, 2024
  • 1 min read

መንግስት ከውጪ ሀገራት የሚወስዳቸው ብድሮች እዳቸው ለትውልድ እንዳይተላለፍ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ተጠየቀ፡፡


ይህ የተጠየቀው መንግስት ከተለያዩ አካላት ጋር የተፈራረመውን የብድር ስምምነት በፓርላማ በስጸደቀበት ወቅት ነው፡፡


የጸደቁት ብድሮች የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም ዓቀፍ የልማት ማህበር ጋር እና ከጣሊያን መንግስት በብድር የሚያገኛቸው ናቸው ተብሏል፡፡


ከዓለም አቀፍ የልማት ማህበር ጋር የተፈረሙት 3 የብድር ስምምነቶች፤ ለንግድ ሎጀስቲክስ ማስፈፀሚያ፣ ለትምህርትና ስልጠና ተግባራት ፐሮጀክት ማስፈጸሚያና ለዲጂታል መታወቂያ አካታችነትና አገልግሎት እንደሚውሉ በመንግስት ተነግሯል፡፡


ከጣሊያን መንግስት የተገኘው ብድር ደግሞ፤ ለኢነርጂ ዘርፍ የበጀት ድጋፍ ይውላል የተባለ ሲሆን በተለይም ከሀገሪቱ የገቢ ንግድ 95% የሚደርሰውን የወደብ አገልግሎት ለሚሰጥው የሞጆ ደረቅ ወደብ መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ይውላል ተብሏል፡፡



መንግስት የሚወስዳቸውን ብድሮች በመጪው ትውልድ ላይ እዳ የሚጭኑ እንዳይሆኑ እና ለትምህርት እና መሰል አገልግሎቶች ለሚወሰዱት ብድሮች ደግሞ አበዳሪ ሀገራት የራሳቸውን አላማ ስላላቸው በሀገሪቱ ባህልና የትምህርት አሰጣጥ ላይ ጫና እንዳይኖራቸው መንግስት ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል የሚልም ሃሳብ ተነስቷል፡፡


መንግስት በበኩሉ ከንግድ ብድሮች ራሴን አቅቤያለሁ፤ አበዳሪ አካላት ገንዘብ ከማበደርና ቴክኒካል ድጋፍ ከማድረግ ውጪ በብድር የሚከወኑ ፕሮጀክቶች የምከታተለውና የማስፈፅመው እኔው ስለሆንኩ የተነሱ ስጋቶች አያሰጉኝም ብሏል፡፡


ማንያዘዋል ጌታሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page