ወረርሽኙንለመከላከል የሚሰጥ ክትባት ቢኖርም ክትባቱን በተለይ ከከተማ ወጣ ወዳሉ ቦታዎች ለማድረስ ዘመናዊ የመድኃኒት ማቆያ አለመኖር ችግሩን አብሶታል ተብሏል።
ለኩፍኝመከላከያ የሚሰጥ ክትባት የቅዝቃዜ መጠኑን ጠብቆ እንዲቆይ የሚያደርጉ ማከማቻዎች እንዲሁም ክትባቱን ለህጻናቱ ለመስጠት የሚያገለግሉ ማስቀመጫዎች እጥረት ችግር መፍጠሩ ተነግሯል።
በአካባቢውምንም አይነት የክትባት እጥረት ባይኖርም የክትባት መድኃኒቶቹ ከዋና ማከፋፈያ ከወጡ በኋላ ወደ ወረዳ ተሰራጭተው ለህጻናቱ እስከሚሰጡ ድረስ ዘመናዊ ማቆያዎች ባለመኖራቸው ችግር መፍጠሩን በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሀዋሳ ቅርንጫፍ ኃላፊ እና የደቡብ ዲስትሪክት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ዘመን ለገሰ ነግረውናል።
የክትባትመድኃኒቶቹ ወደ ሀገር ሲገቡም ሆነ ሲጓጓዙ እክል ባይገጥማቸውም ወደ ወረዳዎች ሲሰራጩ በአያያዝ ጉድለት ይበላሻሉ ተብሏል።
ክትባቱ በሚፈለገው የቅዝቃዜ መጠን ለማስቀመጥ የኃይል መቆራረጥ እና የማቀዝቀዣ እጥረት አለ ተብሏል።
በሲዳማናበቀድሞ ደቡብ ክልል በሚገኙ ወረዳዎች በተከሰተው የኩፍኝ ወረርኝ ለመከላከል የክትባት መድኃኒቱ ቢሰራጭም በአግባቡ ሳይቀመጥ ቀርቶ በመሰጠቱ ለሞት የተዳረጉ ህጻናት መኖራቸውን አቶ ዘመን ናግረዋል።
ከዋናየመድኃኒት ማከማቻ በተጨማሪ በተለይ በወረዳዎች ላይ መድኃኒት ሳይበላሽ እንዲቆይ የሚያደርጉ ማቆያዎች ግንባታና የመሳሪያ ስርጭት ሊሰራበት ይገባል ብለዋል ኃላፊው።
ለዚህም በጤና አገልግሎት ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
በሀዋሳ ከተማ በሚገኘው የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሀዋሳ ቅርንጫፍ እና የደቡብ ዲስትሪክት ለአጠቃላይ መድኃኒት አቅርቦት መሻሻል የተለያዩ ማሻሻያዎች እየከወነ ነው ተብሏል።
ተቋሙ በሀዋሳና በደቡብ ዲስትሪክት ደግሞ አርባምንጭና ነገሌ ቦረና ከ570 በላይ ለሆኑ የግልና የመንግስት የጤና ተቋማት መድኃኒና የህክምና ግብዓት እንደሚያቀርብ ሰምተናል።
በደቡብ ቅርንጫፍ በተለይ ለቲቢ በሽታ መመርመሪያ የሚሆኑ መሳሪያዎች እና መድኃኒት አቅርቦት በUSAID ኢትዮጽያ ከሚገኝ ድጋፍ እንደሚሸፈን ተነግሯል።
ምህረት ስዩም
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments