የኢትዮጵያ መንግስት የንግድ ስርአቱን ለማዘመን ለቀረፀው ፕሮግራም አዲስ የድጋፍ ማዕቀፍ ማዘጋጀቱን የአውሮፓ ህብረት ተናገረ።
የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያን የግል ዘርፍ እና የንግድ ስርአት ለመደገፍ ታስበው የተዘጋጁ መርሃ ግብሮችን ስራ ላይ እዋለ እንደሚገኝ ተናግሯል።
ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ ደግሞ ትኩረቱ የኢትዮጵያ መንግስት የንግድ ስርአቱን ለማዘመን በቀረፀው ፕሮግራም ላይ ማድረጉን፤ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት ፅህፈት ቤት የፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ልዑል ሃብቴ ነግረውናል፡፡
በኢትዮጵያ የግሉ ዘርፍ ሚና በኢኮኖሚው ውስጥ እንዲያድግ ህብረቱ ሶስት ፕሮጀክቶችን ቀርፆ እየሰራ እንደሚገኝም ሠምተናል፡፡
ሶስቱ ፕሮጀክቶች በአጠቃላይ ወደ አስር ሚሊየን ዩሮ በጀት በህብረቱ እንደተያዘላቸው አቶ ልዑል ተናግርዋል፡፡
ህብረቱ ከገንዘብ ድጋፍ ባሻገር ሞያዊ ዕገዛም እንደሚያደርግ አስተባባሪው ተናግረዋል።
ንጋቱ ረጋሣ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comentarios