top of page

መጋቢት 4፣2016 - ከመጠን ያለፉ የካሳ ጥያቄዎች እና መሰል ችግሮች የልማት መሬት አቅርቦት ላይ እክል እየፈጠሩ ነው ተባለ

  • sheger1021fm
  • Mar 13, 2024
  • 1 min read

ከመጠን ያለፉ የካሳ ጥያቄዎች እና መሰል ችግሮች በባለሃብቶች የልማት መሬት አቅርቦት ላይ እክል እየፈጠሩ ነው ተባለ።


በኢትዮጵያ የአውሮፓ ንግድ ምክር ቤት የተዘጋጀውና በባለሃብቶች የልማት መሬት አቅርቦት ላይ ያተኮረ የፖሊሲ ሰነድ ይፋ ሆኗል።


ሰነዱ በተለያዩ የአስተዳደር እርከኖች ያሉ የቢውሮክራሲ መዘግየቶች፣ ቀድሞ የተዘጋጀ የኢንቨስትመንት መሬት አለመኖር፣ ከመጠን ያለፉ የካሳ ጥያቄዎች እና የካሳ አሰጣጥ በተለይም ካሳን በቀጥታ ለህብረተሰቡ ከመፈፀም ይልቅ ወደ መልሶ ማቋቋሚያ ፈንድ ለማስገባት መወሰኑን በመጥቀስ ያሉ ችግሮችን ይዘረዝራል።


ችግሮቹ፤ በክልላለዊ መዋቅር እና በመሬት መስሪያ ቤት ሃላፊዎች ላይ በሚደረጉ ለውጦች፣ በፌዴራል እና በክልል ባለስልጣነት መካከል ባለ የቅንጅት ክፍተት፤ የአስተዳደር ችግር እና በመሳሰሉ ምክንያቶች እንደሚባባሱም ይጠቅሳል።


በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት ለማሳደግ የሚረዳ ምክረ ሃሳብ የያዘ የፖሊሲ ሰነድ እንደሆነ፤ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ንግድ ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ባህሩ ተመስገን ተናግረዋል።


በግብርና ሚኒስቴር የገጠር መሬት አስተዳደር ክፍል ውስጥ የመሬት ህግ ባለሞያ የሆኑት አቶ አበባው አበበ የቀረቡት አብዛኞቹ ችግሮች ያሉ ናቸው ብለዋል።


መሬት አስመልክቶ የተዘጋጀውን ህግ ባለመረዳት ምክንያት የቀረቡም ግን እንዳሉ አክለዋል።


የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንም በፖሊሲ ሰነዱ የተነሱ ጉዳዮች ግብአት ሊሆኑ የሚችሉ ናቸው ብሎናል።


ንጋቱ ረጋሣ



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page