top of page

መጋቢት 30 2017 - የአየር ንብረት ለውጥ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ አሁን ቡና እያበቀሉ ካሉ አካባቢዎች መካከል ከ40 እስከ 60 ከመቶ የሚሆኑ ቡና አብቃይ አካባቢዎች ቡናን ላያበቅሉ ይችላሉ ተባለ፡፡

  • sheger1021fm
  • Apr 8
  • 1 min read

የአየር ንብረት ለውጥ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ አሁን ቡና እያበቀሉ ካሉ አካባቢዎች መካከል ከ40 እስከ 60 ከመቶ የሚሆኑ ቡና አብቃይ አካባቢዎች ቡናን ላያበቅሉ ይችላሉ ተባለ፡፡

 

የአየር ንብረት ለውጥን ኢትዮጵያ ላይ በ2050 ዓመተ ምህረት ላይ በጠቅላላ ምርቷ ላይ 10 ከመቶ የሚሆነው ሊያሳጣት እንደሚችል ጥናት ማሳየቱን ተነገረ፡፡

 

አሁንም 10 ከመቶ የሚሆነው የሀገሪቱ ጠቅላላ ምርት በአየር ንብረት ለውጥ እየታጣ ነው፡፡

 

ይህ እውን እንዳይሆን ከወዲሁ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ እንዳይሆን መስራት ያስፈልጋል ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ የሥነ ምግብ ሽግግር ሥርዓተ የአየር ንብረት ለውጥ አስተባባሪ ከፈለኝ ጌታሁን እንዳሉት የአየር ንብረት ለውጥ በአለማችን በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገራት ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል፡፡

 

በተለይም በግብርናው ዘርፍ ላይ የደቀነው ስጋት አሳሳቢ ነው የሚሉት ከፈለኝ ጌታሁን የአፈር ለምነትን ከማሳጣት ጀምሮ የውሃ አካላትም እንዲደርቁ አየር ንብረት ለውጥ እያደረገ መሆኑን ይህም በጥናት መረጋገጡን ያብራራሉ፡፡

 

ኢትዮጵያ በአመት ከፍተኛ የሆነ የውጪ ምንዛሪ የምታገኝበት የቡና ምርት ቀዳሚው ሲሆን የአየር ንብረት ለውጥ ክፉ ጥላ እንዳይጥልበት ስጋት መደቀኑን ከፈለኝ ጌታሁን ነግነውናል፡፡

 

ከግብርናው ዘርፍ ባለፈም በማህበረሰቡ ጤንነት ላይ የሚያሳድረው ጫና የአየር ንብረት ለውጥ እየጨመረ ሲመጣ የበረታ ነው የተባለ ሲሆን ይህ እውን እንዳይሆን እንደ ሀገር አየር ንብረት ለውጥን የሚከላከሉ ስራዎች መስራት አለብን ሲሉ ይመክራሉ፡፡

 

የኢትዮጵያ መንግስት ባለፉት 10 ዓመታት ከአፈር ውሃ ጥበቃ አንስቶ እየሰራቸው ያሉ የጥበቃ ስራዎች አየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ጥሩ ጅምሮች ናቸው ተብሏል፡፡

 

ታዳሽ ኃይልን መጠቀምና መሰረተ ልማቶች እንደ ሀገር ማስፋፋትም ያስፈልጋል ተብሏል፡፡

 

በረከት አካሉ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

 

 

 

 

 

Comentarii


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page