መጋቢት 30 2017 - ኢትዮጵያ ኢትዮ ኤይድ በሚል ከራሷ አልፋ ለተቸገሩ ጎረቤቶች እርዳታ ታቀርባለች ተብሏል
- sheger1021fm
- Apr 8
- 1 min read
ኢትዮጵያ ለሚያጋጥሙ አደጋዎች ሁሉ በራስ አቅም ምላሽ ለመስጠት በየዓመቱ ከበጀቷ 3 በመቶ ያህል ገንዘብ ለመሰብሰብ እያንዳንዱ ነዋሪ የማዋጣት ግዴታ አለባት ተባለ፡፡
በዚህም ኢትዮ ኤይድ በሚል ከራሷ አልፋ ለተቸገሩ ጎረቤቶች እርዳታ ታቀርባለች ተብሏል፡፡
የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ረቂቅ አዋጅ ላይ በፓርላማው ውይይት ሲደረግ ነው ይህ የተባለው፡፡
ለአደጋ ጊዜ ምላሽ ይሰጣል የተባለው እና በአዋጁ መሰረት ለሚቋቋመው ፈንድ በአመት ከኢትዮጵያ በጀት 3 በመቶ የሚሆን ገንዘብ ይሰበስባል የተባለ ሲሆን ይህም በዘንድሮው የአንድ ነጥብ አምስት ትሪሊዮን በጀት ስናሰላው 45 ቢሊዮን ብር ያስፈልገዋል እንደማለት ነው፡፡

ለዚህም የመንግስት እና የግል ሰራተኛው እንዲሁም የግልና የመንግስት ተቋማት መንግስታዊ ያልሆኑም ድርጅቶች እንዲያዋጡ በረቂቅ አዋጁ በአስገዳጅነት ተደንግጓል፡፡
ከዛም ባለፈ እያንዳንዱ ግለሰብ እንዳቅሙ ማዋጣት ይጠበቅበታል ተብሏል፡፡
ከተቋማት እና ከኢትዮጵያውያን በተሰበሰበው ገንዘብ ጠንካራ የአደጋ ጊዜ ምላሽ የሚሰጥ ተቋም በመመስረትም ኢትዮ ኤይድ በሚል ለጎረቤት አገራትም እንተርፋለን ብሏል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…
ትዕግስት ዘሪሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
📌Spotify : https://shorturl.at/QG8f2
Opmerkingen