መጋቢት 30 2017 - በ5 ተፋሰሶች በ45 ሚሊዮን ዩሮ ለሚተግበር ታቅዶ የነበረው የውሃ ሀብት አስተዳደር ስራ ዛሬ በሶስቱ ወንዞች ላይ ተጀምሯል
- sheger1021fm
- Apr 8
- 1 min read
በ5 ተፋሰሶች በ45 ሚሊዮን ዩሮ ለሚተግበር ታቅዶ የነበረው የውሃ ሀብት አስተዳደር ስራ ዛሬ በሶስቱ ወንዞች ላይ ተጀምሯል፡፡
በተከዜ፣ አባይ፣ አዋሽ፣ ኦሞ ጊቤ፣ ሪፍት ቫሊ ተፋሰሶች ላይ የውሃ ሀብት አስተዳደር ስራ በ45 ሚሊዮን ዩሮ ለመጀመር ታቅዶ ነበር ነገር ግን ዛሬ በአዋሽ ፣ በአባይ እና በተከዜ ተፋሰሶች ላይ የውሃ ሀብት አስተዳደር የማስጀመር ስራ ተካሂዷል፡፡
ፕሮጀክቱ በውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና በውሃ እና መሬት ማዕከል ይተገበራል የተባለ ሲሆን የገንዘብ ድጋፉ ከኔዘርላንድ ኤምባሲና ከአውሮፓ ህብረት የተገኘ ነው ተብሏል፡፡
ፕሮጀክቱ በውሃ ምክንያት የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ለመፍታት ወደ ወንዞች የሚለቀቁ በካዮችን እና ፍሳሽ ቆሻሻዎችን ለመከላከል እና የውሃ ሀብትን በአግባቡ ለመጠቀም ይረዳል ተብሏል፡፡
ፕሮጀክቱ በ5 ዓመት ውስጥ ይከናወናል የተባለ ሲሆን በአስራ አንድ ክልሎች 74 ዞኖች እና 724 ወረዳዎችን እንደሚያካልል ተነግሯል፡፡
የተፋሰስ አስተዳደር ድጋፍ ለጠንካራ ፣ አካታችና ተስማሚ ለውጥ ለኢትዮፕያ ብሔራዊ የውሃ ሀብት አስተዳደር ፕሮግራም ይሰኛል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
📌Spotify : https://shorturl.at/QG8f2
Comments