መጋቢት 30፣2016 - የ1966ቱ አብዮት ከየካቲት እስከ የካቲት፤ ለ 1 ዓመት በየሁለት ወሩ የሚዘክረዉ የዉይይት መድረክ ዛሬ ተጀመረ
- sheger1021fm
- Apr 8, 2024
- 1 min read
የ1966ቱ አብዮት ከየካቲት እስከ የካቲት፤ ለ 1 ዓመት በየሁለት ወሩ የሚዘክረዉ የዉይይት መድረክ ዛሬ ተጀመረ።
መድረኩን ያሰናዱት ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ እና የሰላምና የደህንነት ጥናት ኢንስቲትዩቱ በጋራ በመሆን ነው።
የውይይት መድረኩ እየተካሄደ ያለው በአዲስ አበበ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን የኢትዮጵያን አብዮት በታሪክና በንድፈ ሀሳብ የቃኙ የጥናት ጹሁፎች ቀርቦበታል።
የጥናት ጹሁፉን ያቀረቡት በተባበሩት አረብ ኢሜሬትስ የአፍሪካ ጥናት ተቋም ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ስሜነህ አያሌው እና በብሪስቶል ዩኒቨርስቲ የምርምር ተባባሪ የሆኑት እዮብ ባልቻ ናቸው።
ጥናት አቅራቢዎቹ በአለም በተለያዩ ጊዜያት የተደረጉ አቡዮቶች ተሞክሮ እና የኢትዮጵያ የ1966ቱ አብዮት ለኢትዮጵያ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ያሳደረው ተጸዕኖ ቃኝተዋል።
ያሬድ እንዳሻው
ተቀራራቢ ዘገባዎች
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: @ShegerFMRadio102_1
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments