top of page

መጋቢት 30፣2016 - በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የባህል እና የጥበባት ኢንዱስትሪ ጉባኤ ተጀመረ።

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የባህል እና የጥበባት ኢንዱስትሪ ጉባኤ ተጀመረ።


በ''ሰላም ኢትዮጵያ'' አሰናጅነት ዛሬ  በአዲስ አበባ ዪኒቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ  የተጀመረው ጉባኤው  ነገም ይቀጥላል ተብሏል።


ጉባኤው፤ የኮፒ ራይት እና አእምሮአዊ ንብረት ጥበቃ፣ የጥበባት ትምህርት፣ የባህልና የጥበባት ስራዎች ስርጭትን በተለመከተ ይመከራል ተብሏል፡፡


ጉባኤው የተሰናዳውም፤ በጉዳዮቹ ላይ ከባለሞያዎች ጋር በጥናት የተደገፈ ጥልቅ ውይይት በማድረግ፤ በኢትይጵያ የባህልና የጥበባት ዘርፉ የሚመራበት ስርዓት ለመገንባት እንዲያግዝ ነው ሲሉ  የሰላም ኢትዮጵያ መስራችና ስራ አስኪያጅ አቶ ተሾመ ወንድሙ ተናግረዋል፡፡


''ባህልና ስነ ጥበብ የኢንቨስትመንት ዘርፍ አለመሆን፣ ኪነ ጥበቡ የሚመራበት ፖሊሲ አለመኖር እንዲሁም የቅጅና ተዛማጅ መብቶች ባለሞያዎችን ተጠቃሚ በሚያደርግ መልክ ተግባራዊ አለመደረጋቸው በኢትዮጵያ  ለባህልና ጥበባት እድገት አብይ ችግሮች ናቸው'' ሲባል ሰምተናል፡፡


የአዲስ አበባ ባህል ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ም/ኃላፊ እና የሙዚቃ ባለሞያ ሰርፀ ፍሬ ስብሀት '' በተጠቀሱት ችግሮች ሰበብ የኪነጥበብን የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽነት ሳንጠቀምበት ቀርተናል'' ብለዋል።


በሁለቱ ቀናት ጉባኤ በኪነ ጥበብ ባለሞያዎችና በሚመለከታቸው ባለድርሻዎች በሚቀርቡ ጥናቶችና ዳሰሳዎች ላይ ውይይቶች ይደረጋሉ ተብሏል።


ኤደንገነት መኳንንት



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





ShegerFM: @ShegerFMRadio102_1

Comentarios


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page