top of page

መጋቢት 3 2017 - ዳሸን ባንክ "ሸሪክ ሁኑ" የሚል ፕሮግራም ጀመረ።

ባንኩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶችን ለማገዝ ሸሪክ ሁኑ ሲል የጠራውን ንቅናቄ የጀመረ መሆኑን የተናገረው በትናንትናው እለት ለእስልምና እምነት ተከታይ ደንበኞቹ የኢፍጣር መርሃግብር በሸራተን ሆቴል ባዘጋጀበት ወቅት ነው።


ይህ ንቅናቄ ባንኩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችንና ማህበራዊ ጉዳዮችን ለመደገፍ ያለመ ሲሆን፤ የማህበረሰብ ተሳትፎን ለማሳደግ እንዲሁም ከደንበኞቹ ጋር ያለውን ግኑኝነት ለማጠናከር በማሰብ የተዘጋጀ ነው ብሏል።


በዝግጅቱ ላይ የ #ዳሸን_ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው አለሙ ዳሸን ባንክ ከደንበኞች እሴት እና የፋይናንስ ፍላጎት ጋር የሚጣጣሙ ሸሪዓን ያሟሉ የባንክ አገልግሎቶችን ለማቅረብ ቁርጠኛ ነው ብለዋል።

ሁላችሁም ሼሪክ ሁኑ ፕሮግራም የዳሽን ባንክ ደንበኞች እንደ የሂሳብ መክፈቻ፣ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን እና የፖስ (POS) ግብይቶችን ከዚህ ዓላማ (Model) ጋር ለማስተሳሰር ያስችላቸዋል ተብሏል።


ከየካቲት 2017 ዓ.ም እስከ ሰኔ 2017 የሚቆየው ይህ ንቅናቄ የባንኩን የፋይናንስ አካታችነት እና ማህበራዊ ሃላፊነት የመወጣት ፍላጎት የሚያጠናክር ይሆናል ተብሎለታል ።


ባንኩ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ( #ሸሪክ ) የጀመረበትን 7ኛ ዓመት በቅርቡ አክብሯል።


ይህም ምክንያት በማድረግም ከደንበኞቹ በአደራ መልክ የሰበሰበውን ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ ለ31 ሀገር በቀል የግብረ-ሰናይ ድርጅቶች መስጠቱ ይታወሳል።


ዳሸን ባንክ ካሉኝ አጠቃላይ ደንበኞች ከ1.3 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት የወለድ ነፃ አገልግሎት ደንበኞች ናቸው ብሏል።


ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page