መጋቢት 28 2017 - ‘’አምራች ተቋማት የመሰረተ ልማት ይሟላልን እና ሌሎች ጥያቄ እያቀረቡልኝ ነው’’ የኢዲስ አበባ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ
- sheger1021fm
- Apr 7
- 1 min read
‘’አምራች ተቋማት የውጪ ምንዛሪ አቅርቦት፣ የመስሪያ ቦታ እና ሌሎች የመሰረተ ልማት ይሟላልን ጥያቄ እያቀረቡልኝ ነው’’ ሲል የኢዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ተናገረ።

ቢሮው ክፍተቶች እንዳሉ ጠቅሶ ጥያቄውን ለመፍታት ከተማ አስተዳደሩ ጥረት እያደረገ ነው ብሏል፡፡
ይህ የተባለው ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ትምህርት ኤግዚቢሽን በአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬሽን ማዕከል መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ ከንቲባ አዳነች አበቤ ከተማ አስተዳደሩ አምራች ተቋማት ዋንኛ ትኩረታቸው ተተኪ ምርት ላይ እንዲያተኩሩ እያበረታታን ነው ብለዋል።
ለዚህ የሚሆን አስፈላጊ የሆኑ የፋይንስ እና ሌሎችም ድጋፎችን እያደረ ግን ነው ሲሉ አስረድተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ኢንስዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊና ምክትል ከንቲባ ዣንጥራር አባይ በበኩላቸው መንግስት ለአምራች ተቋማት ድጋፉን ማድረግ እንደሚቀጥል ተናግረው አምራቾች የመሰረተ ልማትና የውጪ ምንዛሪ አቅርቦት ጥያቄ እንደሚያነሱ ጠቅሰዋል።
ለጥያቄው ምላሽ ለመስጠት ተቋማቸው በርትቶ እየሰራ መሆኑን ያስረዱት አቶ ዣንጥራር አሁንም ዘርፉ የበለጠ ድጋፍ ይፈልጋል ብለዋል።
በረከት አካሉ
Comments