መጋቢት 28 2017 - በቅድመ 1 ደረጃ ት/ት ያልጀመሩ ልጆች ከ1 ክፍል በኋላ ባላቸው ትምህርት የሚያስመዘግቡት ውጤት ከተቋማት ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ መሆኑን ጥናት አሳየ
- sheger1021fm
- Apr 7
- 1 min read
በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ያልጀመሩ ልጆች ከአንደኛ ክፍል በኋላ ባላቸው ትምህርት የሚያስመዘግቡት ውጤት ከተቋማት ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ መሆኑን ጥናት አሳየ፡፡
መንግስትም ይህንን ተገንዝቤ የመዋዕለ ህፃናት ትምህርት ቤቶች ብዛት 30 ሺህ አድርሻለሁ ብሏል፡፡
ይህ የግል የትምህርት ተቋማትን እንደማይጨምርም በትምህርት ሚኒስቴር አቶ ዮሴፍ አበራ ነግረውናል፡፡
በድህነት ውስጥ የሚገኙ ወላጆች አቅም በማጣት ምክንያት ልጆቻቸውን የቅድመ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ስለማያስገቧቸው የልጆቻቸው የትምህርት ውጤት ላይ አሉታዊ ተፅኖ እያሳደረ እንደሆነ በጥናቱ ተጠቅሷል፡፡

ጥናቱ ሲጠና የገጠር የከተማ የደሀ እና የሀብታም ወላጆች ልጅን የማስተማር ዘይቤ ተብሎ ተለይቶ እንደተጠምተናል ሰምተናል፡፡
ያንግ ላይቭ የተሰኘውና ጥናቱን ያስጠናው ተቋም የጥናቱን ግኝት ከተመለከተ በኋላ ለመንግስት በማሳወቅ በሁሉም ክልሎች በሚባል ደረጃ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመንግስት በኩል እንዲጀመር መደረጉን የነገሩን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና በጥናቱም ላይ ተሳታፊ የሆኑት ፕ/ር ጣሰው ወ/ሃና ናቸው፡፡
የወላጆች በአቅም መጎልበት ለልጆቻቸው የትምህርት ውጤት ላይ ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል ያሉት ደግሞ በትምህርት ሚኒስቴር የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ክፍል መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑ አቶ ዮሴፍ አበራ ናቸው፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ማርታ በቀለ
Comments