የፍትህ፣ የርትዕ እመቤቷ ‘’ጀስቲሺያ’’፤ የቤት ሰራተኞች መብት እንዲከበር፣ እነሱንም የተመለከተ ህግ እንዲወጣ የግንዛቤ ስራ ለመስራት መጥታለች፡፡
ጀስቲሺያ፤ በቅድስ ይልማ አና አዜብ ወርቁ የተደረሰ ፊልም ነው፡፡
ዳይሬክተሯ ደግሞ ቅድስት ይልማ ነች፡፡
በኢትዮጵያ የቤት ሰራተኞች የሚመሩበት እና የሚተዳደሩበት ህግ የለም፡፡
ሕጉ ባለመኖሩም በቤት ሰራተኞች ላይ የተለያዩ በደሎች እንደሚደርሱ፣ አለፍ ሲልም ራሳቸው ሰራተኞቹም ችግር ፈጥረው እንደሚገኙ የህግ ባለሞያ ሴቶች ማህበርለ ለሸገር ነግሯል፡፡
ጀስቲሺያ፤ የቤት ሰራተኞን የተመከተ የህግ ማዕቀፍ አንዲወጣ ግንዛቤ መፍጠርን ዓለማ ይዞ መሰራቱን ሰምተናል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
ShegerFM: @ShegerFMRadio102_1
Comments