top of page

መጋቢት 28፣2016 - ከህዳሴው ግድብ የሚመነጨው ሀይል ለተጠቃሚዎች መቼ ይደርሳል?

ግንባታው ከተጀመረ 13 ዓመት የሆነው የህዳሴው ግድብ ስራው በመጪው አመት እንደሚጠናቀቅ ተነግሯል፡፡


ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ 5150 ሜጋ ዋት ሀይል ያመነጫል ተብሏል፡፡


ባለሙያዎች ምንም እንኳን ፕሮጀክቱ ግንባታው እየተጠናቀቀ ቢሆንም የመነጨውን ሀይል ከየሰው ቤት ማድረስ ትልቅ አቅም የሚጠይቅ ነው ይላሉ፡፡


ሀይል የማመንጨቱን ያክል የማስተላለፊያ መሰረተ ልማት ግንባታውንም ሊታሰብበት ይገባል ሲሉ ይመክራሉ፡፡

ለመሆኑ በዚህ ዙሪያ ምን እየተሰራ ነው?


ንጋቱ ረጋሣ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





ShegerFM: @ShegerFMRadio102_1

Comments


bottom of page