በዩኔስኮ በማይዳስ ቅርስነት የተመዘገበውና የሲዳማ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ የሆነው የፊቼ - ጫምበላላ በዓል ዛሬ በሀዋሳ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።
በዓሉን ለማክበር ከተለያዩ አካባቢዎች በቦታው የተገኙ እንግዶች ቁጥር ከሌላው ጊዜ የበለጠ እንደሆም ተነግሯል።
ይህም የክልሉን የቱሪዝም ዘርፍ የሚያነቃቃ ነውም ተብሏል።
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ''የሲዳማ ብሔረሰብ በፊቼ -ጫምበላላ በዓል ለተፈጥሮ እፅዋትና ስነ ምህዳር ልዩ እንክብካቤና ጥበቃ የሚደረግና የሴቶችና ህፃናት መብት የሚከበርበት ወቅት ሲሆን ለደን፣ ለአፈና ለውሃ ጥበቃ እንዲሁም ለተፈጥሮ የሚሰጠው ክብር የላቀ ነው'' ሲሉ ተናግረዋል።
''እነዚህ ባህላዊ እሴቶች ተተንትነው ፊቼ -ጫንባላላን በአለማቀፍ ቅርስነት እንዲመዘገብ ካስቻሉት ነጥቦች የተወሰኑቱ ናቸው'' ብለዋል በዓሉ በሚደረግበት መድረክ ላይ።
ሀዋሳ የፊቼ -ጫምባላላ በዓልን ለማክበር ቀድማ ስትዘጋጅ እንደቆየችና ከትናንትና ጀምሮ በተለያዩ ክዋኔዎች በዓሉን በድምቀት እያከበረች እንደሆነ የሲዳማ ክልል የኮምዩኒኬሽን ቢሮ ምክትል ሀላፊ እያሱ ዳዊት ለሸገር ነግረዋል።
የሲዳማ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል የሆነው ''ፊቼ - ጫምበላላ'' በዩኔስኮ በማይዳስ ቅርስነት የተመዘገበው እ.አ.አ በ2015 ነው።
ማንያዘዋል ጌታሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
ShegerFM: @ShegerFMRadio102_1
תגובות